Ethiopian Tomato Recipe ቲማቲም ለብለብ Timatim Lebleb
Melegna | መለኛ
0:00 / 0:00
Ethiopian Tomato Recipe ቲማቲም ለብለብ Timatim Lebleb
14 475 просмотров · 10 мес. назад
Melegna | መለኛ
195 тыс. подписчиков
14 475 просмотров · 10 мес. назад
የዛሬው የቲማቲም ለብለብ ለሁለት ሰው በቂ አንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀ ነው ፡፡ በዛ አድርጋችሁ ማዘጋጀት እና ማቅረብ ከፈለጋችሁ የግብዓት መጠኑን ከፍ አድርጉ፤ ይህ ምግብ ቶሎ የሚደርስ ነገር ስትፈልጉ እና በፆም ወቅት ልዩ የሆነ አማራጭ ነው፡፡ ትንሽ ቃጠል እንዲያደርግ አድርጋችሁ ካዘጋጃችሁት የበለጠ ጣፋጭ ይሆናል፡፡ እራሱን ችሎ እና ከተለያዩ የፆም እና የፍስግ ምግቦች ጋር እንደ አይነትም አድርጋችሁ ማቅረብ ትችላላችሁ ፡፡
የግብዓት አይነት እና መጠን
5 ታጥቦ ፍሬው ወጥቶለት በቀጨኑ የተከተፈ ቲማቲም
1 ራስ ቀይ ሽንኩርት
1 ከነፍሬው የተከተፈ አረንጓዴ ቃሪያ
1 የባሮ ሽንኩርት
6 ፍሬ ነጭ ሽንኩርት
5 የሾርባ ማንኪያ የምግብ ዘይት
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ከሙን
ግማሽ የሻይ ማንኪያ ጥቁር ቁንዶ በርበሬ
1 የሻይ ማንኪያ የሮዝሜሪ ዱቄት
1 የሻይ ማንኪያ ሚጥሚጣ
የምትፈልጉትን ያህል ጨው
ማባያ
ዳቦ
እንጀራ
ቂጣ