Перейти к содержимому

እንኳን በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን አሜን ። ሶል ፎቶ

Sol foto

0:00 / 0:00

እንኳን በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን አሜን ። ሶል ፎቶ

120 просмотров · 2 недели назад
Sol foto
876 подписчиков
120 просмотров · 2 недели назад
እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላምና በጤና በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን! ​"ጊዜያትንና ዘመናትን ይለውጣል፤ ነገሥታትን ያፈልሳል፣ ነገሥታትንም ያስነሣል፤ ጥበብን ለጠቢባን፣ ዕውቀትንም ለአስተዋዮች ይሰጣል።" (ዳንኤል 2:21) ​በዚህ አዲስ ዓመት አዲስ ተስፋ ይዞልን የሚመጣውን ዘመን ከእግዚአብሔር ጋር የምንጀምርበት፣ ከእርሱም ጋር ይበልጥ የምንቀራረብበት ይሁንልን! ያለ እርሱ ምርጫም ሆነ አማራጭ እስከማይኖረን ድረስ እግዚአብሔርን ብቻ የምንከተልበት ዘመን ይሁን። ​በአዲሱ ዓመት እጃችሁ ለመቀበል ሳይሆን ለመስጠት ይዘርጋ፤ እግዚአብሔርም የምትሰጡትን አይንሳችሁ። ይስሐቅ ከእናቱ ሞት በኋላ በርብቃ እንደተጽናና፣ ባለፈው ዓመት ካዘናችሁበት ነገር ሁሉ የምትጽናኑበትን መልካም ነገር እግዚአብሔር ይስጣችሁ። ​እግዚአብሔር የእናንተ የሆነውን ነገር ሁሉ ይባርክልዎ፤ የለፋችሁበትንና የደከማችሁበትን ፍሬ የምትቀበሉበት ዓመት ያድርግላችሁ። የማያውቋችሁ አይተው ይውደዷችሁ፤ የሚሰሟችሁም ያክብሯችሁ። ከከንቱ ድካምና ከፍሬ-አልባ ሥራ ይጠብቃችሁ፤ "በቀረብኝ" የማያሰኝ፣ የማትቆጩበትን ሙሉ ደስታ ይስጣችሁ። ​ከሁሉ በላይ ደግሞ ለእግዚአብሔር የልብ ሀሳብና ለቅዱስ መንግሥቱ ያብቃችሁ! ያብቃን አሜን አሜን አሜን ሶል ፎቶ ​🌻 ​🌻 መልካም አዲስ ዓመት! 🌻 መልካም አዲስ አመት🌻🌻🌻🌻🌻