Перейти к содержимому

#ምን ተሻለኝ!ፈረንጁ ባለቤቴ 3 ኛ ሚስቱ እንደሆንኩ ያወኩት ሀገሩ ሲወስደኝ ነበር! በተደጋጋሚ እየማገጠ ይቅርታ ይለኛል‪@shegerinfo‬ Ethiopia

SHEGER INFO

0:00 / 0:00

#ምን ተሻለኝ!ፈረንጁ ባለቤቴ 3 ኛ ሚስቱ እንደሆንኩ ያወኩት ሀገሩ ሲወስደኝ ነበር! በተደጋጋሚ እየማገጠ ይቅርታ ይለኛል‪@shegerinfo‬ Ethiopia

47 700 просмотров · Трансляция закончилась 9 мес. назад
SHEGER INFO
660 тыс. подписчиков
47 700 просмотров · Трансляция закончилась 9 мес. назад
ምን ተሻለኝ! ፈረንጁ ባለቤቴ 3 ኛ ሚስቱ እንደሆንኩ ያወኩት ሀገሩ ሲወስደኝ ነበር! ሁለት ከወለድኩለት በኋላ ግን አራተኛ ሚስት ይዞ ህይወቴን አመሰቃቀለው ! በተደጋጋሚ እየማገጠ ይቅርታ ይለኛል! በቃኝ እንፋታ ብዬ ጉዳዬን ወደ ፍ/ቤት ስወስደው ወዲህ ጥቁር በመሆኔ ወዲህ የሱ መሰሪነት ግራ አጋብቶኛል ምን ተሻለኝ! ከ ባለቤቴ ጋር የተዋወቅነው በ 2009 በ ፈረንሳይ ፓሪስ ነበር ፡፡ እኔ ከ ኢትዮጵያ ሄጄ ስራ እና ኑሮ ከጀመርኩ 5 ዓመታትን አስቆጥሬ ነበር እሱ ደግሞ ዜግነቱ ጀርመናዊ ሲሆን የራሱ ካምፓኒ ስላለው ፈረንሳይ ሀገር ለ 6 ወር ኮንትራት ስራ ይዞ በመጣበት ጊዜ ነው ፡፡ የትውውቃችን አጋጣሚም በ አንድ መዝናኛ ስፍራ ውስጥ ከ ጓደኛዬ ጋር ሆነን እሱም ከ ጓደኛው ጋር ሆኖ ፑል ስንጫወት ነበር.. በዚያው ወደቤታችን በመኪናቸው ሸኙን ከዛም አልፎ አልፎ መደዋወል እና መገናኘት ጀመርን እሱ በ እድሜ 25 ዓመት ይበልጠኛል በቀደመ ትዳሩ አንድ ልጅ እንዳለው እና ከልጁ እናት ጋርም እንደተለያየ ነገረኝ ለኔ በጣም መልካም ሰው ነበር ይከባከበኛል ሁሌም አርብ ወደ ሀገሩ ሄዶ እሁድ ነበር የሚመለሰው እና ሲመጣ የተለያዩ ስጦታዎችን ይዞልኝ ይመጣ ነበር በዚህ ሁኔታ ላይ ሆነን በድንገት እኔ አረገዝኩ ይህን ሲሰማ በጣም ተደሰተ እንደሚወደኝ እና ሊያገባኝ እንደሚፈልግ ተናገረ ወዲያው ለቤተሰቦቹም ስለ እኔ ነገራቸው እነሱም በደስታ ተቀበሉኝ እኔንም ልጄንም ይዞ አገሩ ይዞኝ መሄድ እንደሚፈልግ ነገረኝ እኔ ደግሞ ያሳየኝ የነበረው እንክብካቤ እና ፍቅር የተለየ ቢሆንም መልካምነቱ ቢገዛኝም ስለሱ ብዙም ስለማላውቅ ፈራው እናም ፈረንሳይ ያሉ የቅርብ ወዳጆቼን አማከርኩ ተይ ይቅርብሽ እዚሁ ደህና ስራ አለሽ ስራሽን ለቀሽ እሱን ተከትለሽ ሄደሽ ችግር ላይ እንዳትወድቂ አሉኝ እኔም እኔ የ3 ወር እርጉዝ ሆኜ የስራ ኮንትራቱን ጨርሶ ከ ፈረንሳይ ቢወጣም በየሳምንቱ እኔጋር ይመጣል እኔም በደንብ እንኳን ሳላውቀው ተከትዬው ላለመሄድ ልጄን ፈረንሳይ ሀገር ሆኜ ወለድኩ ለ ሀገሩ ኢንባሲ አሳውቆ ስለነበር ልጄ እንደተወለደ የ ጀርመን ዜግነት እና ፓስፖርት ተሰጠው በዚህ ጊዜ ቤተሰቦቹ ለምን አትመጣም እና እዚህ ተጋብታችሁ አትኖሩም አሉ እኔም ልጄ ከ አባቱ ጋር እንዲያድግ ብዬ የ 1 አመት ልጅ ሆኖ ጀርመን ገባሁ እዛ ግን የጠበቀኝ ፍፁም ያልጠበኩት ነገር ሆነ እኔ ሶስተኛ ሚስቱ ነበርኩ ከ መጀመሪያ ሚስቱ ጋር ፍቺ ቢያደርግም ከ 2 ኛ ሚስቱ ጋር ግን ገና አልተፋታም ነበር በጣም ደነገጥኩ እንዴት ብዬ አዘንኩ በቃ አልፈልግም ወደ ፈረንሳይ እመለሳለው ስለው በ መጀመሪያ እግሬ ላይ ወድቆ ለመነኝ አሻፈረኝ ስል ግን አንቺ መሄድ ትችያለሽ ልጄን ግን ይዘሽ ከ ሀገር መውጣት አትችይም አለኝ ልጄን ትቼ እንዴት ብዬ ቀረሁ ከ ሁለተኛ ሚስቱ ጋር ፍቺ ፈፀመ በጣም ብዙ እዳ ውስጥ ገብታ ስለነበር ለ ብዙ ጊዜ እዳ ከፈልን ከዛም ጥሩ ኑሮ መኖር ጀመርን ልጄ ብቸኛ እንዳይሆን ሁለተኛ ልጅ መውለድ እንደምፈልግ ተነጋግረን ሁለተኛ ልጅን እንደወለድኩ በ 3 ወሬ መጋባት አለብን አለኝ አኔ ደግሞ በትውልድ ሀገሬ በ ኢትዮጵያ ውስጥ በቤተሰቦቼ ፊት በሥርዓት መጋባት እፈልግ ነበር። ነገር ግን ባለቤቴ እና ቤተሰቦቹ በፈጠሩብኝ ጫና ምክንያት በ ሀገሩ በሲቪል ሥርዓት ለመጋባት ተስማማሁ። ሰርጉ የተከናወነው ቅዳሜ እና እሁድ ቦታ ባለመገኘቱ ሰርጋችን ሀሙስ ነበር ፡፡ ተፈራርመን በ አንድ ሬስቶራንት ውስጥ ምሳ በልተን ወደ ቤት ገባን በ ትዳሬ ደስተኛ ነበርኩ ባለቤቴ ጠንክሮ የሚሰራ፣ ቤተሰቦቼን የሚያከብር እና ልጆቹን የሚወድ ሰው ነበር። በዚህ መካከል አንድ ቀን ድንገት ቢሮው ስሄድ ያላሰብኩት ገጠመኝ ያመንኩት ባለቤቴ ከ ፀሀፊው ጋር ደስ የማይል ነገር እያደረገ ነበር ወዲያው ወደ ቤት ተመለስኩ ተክትሎኝ መጣ እንዴት እንዲህ ታደርጋለህ ብዬ በጣም ተናደድኩ ወንድሙን እና ባለቤቱን ጠርቼ የሆነውን ነገርኳቸው እና መለያየት ነው የምፈልገው አልኩ እሱም በመጀመሪያ ዋሸ በኋላም አምኖ ተሳስቻለው ይቅርታ አለኝ እኔም ይቅርታውን ተቀብዬ ኑሮዬን ቀጠልኩ አመል አለቅ ብሎ ከ ዓመታት በኋላ ደግሞ ከ ሌላ ሴት ጋር ግንኙነት መጀመሩን ደረስኩበት አሁንም ደግሞ ይቅርታ ሲል አሁንስ በዛ ብዬ አሻፈረኝ አልኩ በቃ እንለያይ ስል እሱ ሊፈታኝ አልፈለግም በዚህ ጊዜ እኔ ጉዳዩን ወደ ፍ/ቤት ወሰድኩት ፡፡ በዚህ ጊዜ ከ ጋራ የባንክ ሂሳባችን ላይ እኔን እንዳስወጣኝ ከባንክ ደወሉልኝ እንዴት ይሆናል ብዬ ስጠይቅ ሁለት ሲስተም እንዳለ እና እሱ የፈለገውን ማስገባት እና ማስወጣት እንደሚችል ነገሩኝ እኔ ይህን አላውቅም ነበር ፡፡ በጋራ ያፈራናቸውን ንብረቶችን በመደበቅ ብዙ ገንዘብ ወሰደ ፍ/ቡት ሲጠየቅ አብረን ያፈራነውን ንብረት ለብቻዬ ነው ያፈራሁት እሷ ንብረቴን አይታ ነው ከ ሀገሯ ያመጣኋት እኔ ነኝ እያለ ይናገራል እሱ ዜጋ ስለሆነ የሚታመነው እሱ ነው እኔ ገንዘቡን አውጥቼ እንዳልጠቀም ለልጆቻችን የተቀመጠውን ገንዘብ ሁሉ ያለ ፍቃድ ወስዷል ፡፡ ፍ/ቤቱ እኔ ልጆቼን ይዤ እንድቀመጥ እሱ ደግሞ እንዲወጣ ተወሰነ። በዚህ ጊዜ የልጆቹን ቀለብ እንዲከፍል ቢወሰንበትም ለ 3 ወር ከከፈለ በኋላ ለመክፈል ፈቃደኛ አይደለም ። አሁን ከ ጀርመን ወጥቶ ቤልጂየም ከ አዲሷ ፍቅረኛው ጋር ከ እኔ ጋር ሰርተን ባፈራነው ገንዘብ ቤት ገዝቶ እየኖረ ነው ፡፡ ለ ልጆቼ ግን ከ አንድ ዓመት በላይ ችግር ውስጥ ከወደቀች እኔ ጋር ትመጣለች ወይም ይቅር ትለኛለች በሚል የልጆቹን ተቆራጭ ከ አንድ /ኣመት ተኩል በላይ አልሰጠም ጠበቃዬም እያገዘችን አይደለም ምን ተሻለኝ ! ፡፡ ይሁን ሁሉ የሚያደርገው እንዳልፈታው ሲቸግራት ይቅር ትለኛለች በሚል ነው ይህን ደግሞ ለኔው ብሎኛል እኔ ግን በተደጋጋሚ እየማገጠ ሁሌ ተሳስቼ ነው ይቅርታ እያለ እንዴት ባሌ ነው ብዬ አብሬው ልኑር ይህን መቀበል አልቻልኩም ምን ተሻለኝ ! Sheger Info Media brings, social, economic, political and cultural issues to its audience. Let us know what you think about the specific shows we put forth by commenting down below. Thank you for watching! Like share and subscribe to get the latest Ethiopian News, Information and updates. Ethiopia news | Eritrea news | Amhara | Tplf | Eritrea news | Abiy Ahmed | Tigray news | Metekel | Tigrai news | Amhara news | #Ethiopia #ShegerInfo #MeseretBezu