የሚገርም ጸጋ - ክናንያ || Yemigerim Tsega - Chenaniah
Chenaniah Ethiopia и illasha fekadu
0:00 / 0:00
የሚገርም ጸጋ - ክናንያ || Yemigerim Tsega - Chenaniah
60 856 просмотров · 7 дней назад
Chenaniah Ethiopia и illasha fekadu
60 856 просмотров · 7 дней назад
ነገር ግን ኢየሱስ መካከለኛ የሆነበት ኪዳን ከቀድሞው እንደሚበልጥ ሁሉ፣ የተቀበለውም አገልግሎት ከእነርሱ አገልግሎት ይበልጣል፤ ይህም የተመሠረተው በተሻለ የተስፋ ቃል ላይ ነው። የመጀመሪያው ኪዳን ምንም ጕድለት ባይገኝበት ኖሮ፣ ለሁለተኛው ስፍራ ባልተፈለገም ነበር።
ዕብራውያን 8:6-7
የእኔ የነበረውን ፍርድ ሁሉ
ኢየሱስ ተሸክሟል በመስቀሉ
በአንድ አካል አብሬው ሆንሁኝ
በሥጋው ተጠቀለልሁኝ
ሞቴን ጭልጥ አድርጎት
ትንሳኤውን ተካፋይ ሆንሁኝ
አሁን የቀረኝ ማያልቅ
ያተረፈልኝ ንብረት
የአብ የአባቱ ፍቅር
ኢየሱስን የወደደበት
ፍርዴን ወስዶ ምህረት
ፍዳዬን ወስዶ ፍፁም ረፍት
ጭንቄን ወስዶ ሰላሙን
ፍርሃቴን ወስዶ ፍቅሩን
ሁሉ እንዲሆንልኝ በልጁ
ሁሉ እንዲህ ሆነልኝ በልጁ
እጣዬ ታሰረ ከልጁ
ፍፃሜዬ አማረ በልጁ
እግዚአብሄር አብ ፍቅሩን የገለጠበት
በደም የተፈረመ ሠነድ የምህረት
የኢየሱስ ሥጋ ተቆርሶ
ደሙ ለአዲሱ ኪዳን ፈስሶ
እግዚአብሄር ምሎ ታርቆኛል
ምን ያሠጋኛል
የተበደለው አባቴ
የዕርቅ ምግቡን ሰጥቶኛል
ልጁን አንዴ በልቼ
የዘልዓለም ህይወት ሆኖኛል
የሚገርም ኪዳን ነው የሚገርም
የሚገርም ጸጋ ነው የሚገርም