Перейти к содержимому

ድብቁን ወረርሽኝ፣ በጊዜ ለይተን እንወቅ!November 2 2026

The wisdom media Dr Demissie TD

0:00 / 0:00

ድብቁን ወረርሽኝ፣ በጊዜ ለይተን እንወቅ!November 2 2026

166 просмотров · 1 дн. назад
The wisdom media Dr Demissie TD
11,3 тыс. подписчиков
166 просмотров · 1 дн. назад
በባሕሩ ገጽ ላይ ጎልቶ የታየው፣ ጥቂቱ ጫፍ ብቻ የበረዶው ክምር፣ ከሥሩ ተደብቆ በውኃው ጥልቀት፣ ግዙፉ አለት አለ የማይታይ ሚስጥር። ያ የታወቀው የዓይነት ሁለት ጣጣው፣ በምርመራ ወጥቶ ከላይ የተገለጠው፣ ከሥሩ ግን አለ «ቅድመ ስኳር» ሆኖ፣ በውቅያኖስ ጥልቀት ስንቱን አጥምዶ። የጥያቄ ምልክት የኔም ጭምር ድርሻ፣ ሳላውቀው ስኖርበት በድብቅ ወረርሽኝ፣ በደሜ ውስጥ ሰርጎ ምልክት ሳይሰጥ፣ ጥላውን ጥሎብኝ በዝምታ ጤናዬን ሰረቀኝ። የበረዶው ክምር አስተምሮን ዛሬ፣ ከሚታየው ይልቅ ስውሩ ይከብዳል፤ ሳይቃጠል በቅጠል ቀድሞ መመርመር፣ ሕይወትን ከማዕበል በጊዜ ይታደጋል። ምግቡን እናስተካክል እንቅስቃሴን እናብዛ፣ የጤናን መንገድ ሳንዘገይ እንከተል፤ የተሰወረውን አውቀን ካስቀረነው፣ የሕይወት መርከባችን በሰላም ይሻገራል።