የጆሴፍ አዮ ባባሎላ የህይወትና የአገልግሎት ታሪክ #የእግዚአብሔርጀነራሎች #መንፈስቅዱስ #ተሀድሶ #የእግዚአብሔርክብር
የእግዚአብሔር ጄኔራሎች The God's Generals
0:00 / 0:00
የጆሴፍ አዮ ባባሎላ የህይወትና የአገልግሎት ታሪክ #የእግዚአብሔርጀነራሎች #መንፈስቅዱስ #ተሀድሶ #የእግዚአብሔርክብር
411 просмотров · 3 недели назад
የእግዚአብሔር ጄኔራሎች The God's Generals
545 подписчиков
411 просмотров · 3 недели назад
🔥 የእግዚአብሔር ጀነራሎች — ታሪክን የቀየሩ የእምነት ሰዎች 🔥
በየዘመኑ እግዚአብሔር ለዓለም የሚያሳያቸው ልዩ ሰዎች አሉ ደግሞም ነበሩ። እነሱ ፍጹማን ሰዎች አልነበሩም፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ራሳቸውን ሰጡ፣ በእምነት ቆሙ፣ በጸሎት ተጋደሉ፣ በመንፈስ ተነሳሱ፣ እና የእግዚአብሔር ሥራ በሕይወታቸው እንዲታይ ፈቀዱ።
“የእግዚአብሔር ጀነራሎች” ስንል የምንናገረው ስለ ታላላቅ ስሞች ብቻ አይደለም። ስለ እምነት፣ ስለ ጸሎት፣ ስለ መስዋዕትነት፣ ስለ ጽናት፣ ስለ ታማኝነት እና እግዚአብሔርን ከሁሉ በላይ ስለመፈለግ ነው። እነዚህ ሰዎች በቀላሉ ወደ ከፍታ አልደረሱም። ብዙዎቹ በድካም፣ በተቃውሞ፣ በድህነት፣ በብቸኝነት፣ በአለመረዳት እና በብዙ ፈተናዎች ውስጥ አልፈዋል። ሆኖም ግን ዓይናቸውን በሰው ላይ ሳይሆን በእግዚአብሔር ላይ ብቻ አደረጉ።
🙏 እነሱ የጸሎትን ኃይል ተረዱ፤
🔥 እነሱ የእምነትን ኃይል አወቁ፤
📖 እነሱ ቃሉን ከሕይወታቸው ጋር አዋሃዱ፤
🕊️ እነሱ የመንፈስ ቅዱስን መሪነት ፈለጉ ተጠሙ፤
❤️ እነሱ ነፍሳት እንዲድኑ እና ሰዎች ወደ ክርስቶስ እንዲመጡ ተመኙ እንዲሁም በመንፈስ ቃተቱ።
የእነርሱ ታሪክ የትናንት ታሪክ ብቻ አይደለም። ዛሬም ለእኛ መልዕክት አለው። ምናልባት አንተ ዛሬ የምትገኝበት ሁኔታ ከባድ ሊሆን ይችላል፤ ምናልባት ሕልምህ የማይፈጸም ይመስልህ ይሆናል፤ ምናልባት ጸሎትህ መልስ እንዳላገኘ ይሰማህ ይሆናል፤ ምናልባትም ሰዎች አይረዱህም ይሆናል።
ነገር ግን የእነዚህን የእምነት ሰዎች ታሪክ ተመልከት። ብዙዎቹ የጀመሩት በትንሽ ነገር ነበር። አንዳንዶቹ ማንም ሳያውቃቸው በጸሎት ክፍል ውስጥ ተንበረከኩ፤ አንዳንዶቹ በትንሽ ቦታዎች ጀመሩ። ነገር ግን ታማኝነታቸው ትልቅ ተጽዕኖ አመጣ።
እናም ይህ ትልቁ ጥያቄ ነው፦
እግዚአብሔር በእኔ ትውልድ ውስጥ ምን ሊያደርግ ይችላል?
ምናልባት እግዚአብሔር የሚጠቀምብህ ሰው እንድትሆን እየጠራህ ይሆናል፤ ምናልባትም የመጀመሪያው እርምጃ ብዙ ሰዎች እንዲያዩህ አና እንዲቀበሉህ መሆን ሳይሆን፣ በምስጢር የምታሳልፈው የጸሎት ሕይወት እንዲጠነክር ነው።
ጀነራል የሚኮነው መድረክ ላይ ስለቆምን ብቻ አይደለም፤ በምስጢር ለእግዚአብሔር ታማኝ ስለሆንን እንጂ።
የእግዚአብሔር ጀነራሎች ታሪኮች እነርሱን እያነሳን እንድንደነቅ ብቻ አይደለም የሚሰራው። እኛም እንድንነሳ፣ እንድንጸልይ፣ እንድናምን፣ እንድንጸና እና ለእግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ እንድንሰጥ የሚያስታውሱን እንጂ።
🔥 ትውልድህ የጸሎት ሰዎችን ይፈልጋል!
🔥 ትውልድህ በእምነት የሚቆሙ ሰዎችን ይፈልጋል!
🔥 ትውልድህ እውነትን የሚናገሩ ሰዎችን ይፈልጋል!
🔥 ትውልድህ ራሳቸውን ሳይሆን ክርስቶስን የሚያሳዩ ሰዎችን ይፈልጋል!
ስለዚህ ይህን ታሪክ በመመልከት ብቻ አትቁም። አንተም የራስህን የእምነት ታሪክ ጀምር። የሚቀጥለው የእግዚአብሔር ጀነራል ማን እንደሚሆን አናውቅም። ግን እግዚአብሔር ዛሬም ለራሱ ሰዎችን እየፈለገ ነው።
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ካልዕ 16:9 (AMH)
⁹ እግዚአብሔር ልቡ በእርሱ ዘንድ ፍጹም የሆነውን ያጸና ዘንድ ዓይኖቹ በምድር ሁሉ ይመለከታሉና።
🙏 ከታሪኮቹን እንማር!
📖 ቃሉን እናንብብ!
🔥 በጸሎት እንትጋ!
🕊️ መንፈስ ቅዱስን አጥብቀን እንፈልግ(እንጠማ)!
❤️ ክርስቶስን እንውደድ!
💪 በእምነት እንፅና!
🌍 በትውልድህ ላይ በረከት እንሁን!
የእግዚአብሔር ጀነራሎች — ታሪክን መተረክ ብቻ አይደለም ይልቁንም ከታሪካቸው እንማራለን፣ እምነታቸውም እንድንነሳ ያነሳሳናል። 🔥🙏
ይህ ይዘት እንዲደርስ ለሚፈልጉት ሰው Share ያድርጉ፣ Follow ያድርጉ፣ እና በኮሜንት ውስጥ “እኔም ለእግዚአብሔር እገኛለሁ” ብለው ይጻፉ። 🙏🔥
#የእግዚአብሔርጀነራሎች #GodsGenerals #እምነት #ጸሎት #መንፈስቅዱስ #ክርስቶስ #ወንጌል #ክርስቲያን #ኢየሱስ #Jesus #Christianity #Faith #Prayer #HolySpirit #Gospel #Revival #የመንፈስቅዱስኃይል