Перейти к содержимому

ዲሲፕሊንን ማዳበር | Dr. Eyob Mamo | "አንድን ነገር መጀመር ይቀለኛል፣ ከጀመርኩ በኋላ ግን መቀጠል ያቅተኛል" | በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

Dr. Eyob Mamo

0:00 / 0:00

ዲሲፕሊንን ማዳበር | Dr. Eyob Mamo | "አንድን ነገር መጀመር ይቀለኛል፣ ከጀመርኩ በኋላ ግን መቀጠል ያቅተኛል" | በዶ/ር ኢዮብ ማሞ

21 826 просмотров · 2 г. назад
Dr. Eyob Mamo
45,4 тыс. подписчиков
21 826 просмотров · 2 г. назад
ዲሲፕሊንን ማዳበር • ዲሲፕሊን ማለት አንድን ማድረግ ያለብኝን ነገር ስሜቴ ቢፈቅድም ባይፈቅድም መደረግ ስላለበት ብቻ ማድረግ ማለት ነው፡፡ • በተጨማሪም፣ አንድን መደረግ የሌለበትን ነገር ስሜቴ ቢፈልገውም መደረግ ስለሌለበት ብቻ አለማድረግ ማለት ነው፡፡ • ማንኛውም ችሎታና ብቃት ከዲሲፕሊን ውጪ ከንቱ ነው፡፡ 1. የምትፈልገውን እወቅ • ማከናወን የምትፈልገውንና ጊዜህን ልትሰዋለት የሚገባህን ተግባር በግልጥ እወቅ፡፡ ይህ ቀዳሚና እጅግ ወሳኝ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ • ማንነቴ የሚፈልገውን በሚገባ ሳላውቅ ማንነቴን ለመምራት መሞከር ጊዜን ማባከን ነው፡፡ • ዲሲፕሊን ማዳበር እንዳለብህ የምታስበው ፍላጎትህ ወይም ዓላማህ ምንድን ነው? 2. ለፈለከው ነገር የሚመጥነውን ልማድ ለይተህ እወቅ • እያንዳንዱ ለማዳበር የምትፈልገው ነገር የራሱ የሆነ ባህሪይ አለው፡፡ • ለዚያ ለማዳበር ለምትፈልገው ነገር ምን አይነት ልማድ ብታዳብር ስኬታማ እንደምትሆን ማወቁ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ • ለጠቀስከው ዓላማ የሚያስፈልጉት ዲደሲፕሊኖች ምን ምን ናቸው? 3. ጀምር፣ ከጀመርክ ደግሞ አታቁም • ለማዳበር የምትፈልገውን ነገር መተግበር ጀምር፣ ለነገ አታስተላልፈው፡፡ ሆኖም መጀመር ብቻ በቂ እንዳልሆነም አስታውስ፡፡ • የጀመርከውን ነገር ለማቆም ምንም አይነት ምክንያት አትስጥ፡፡ ውጤት እስከምታገኝ ድረስ ቀጥል፡፡ #discipline #selfimprovement #selfawareness