ከ አንድ ትንሽዬ ገጠር ውስጥ እስከ አለም አቀፍ ሳይንቲስት እስከመሆን | NASA | Tilaye Tadese | Space Exploration
Yomtech
0:00 / 0:00
ከ አንድ ትንሽዬ ገጠር ውስጥ እስከ አለም አቀፍ ሳይንቲስት እስከመሆን | NASA | Tilaye Tadese | Space Exploration
3 547 просмотров · 3 г. назад
Yomtech
1,13 тыс. подписчиков
3 547 просмотров · 3 г. назад
ከ ከብት እረኝነት እስከ አለም አቀፍ የ ናሳ ሳይንስትነት
ከ ሱስ እስከ ናሳ
ቤተሰብ መክፍልም መርዳትም እየቻለ የ ትምህርትን ጥቅም ባለመረዳት ብቻ ትምህርትህን አቁም እያሉ አባት ይቆጣሉ፣ ልጅም በ እምቢተኛነቱ ይቀጥላል፣ አባትን ላለማስከፋት ጥረት ያደርጋል፣ ከ ሚኖርበት የ ገጠር ቀብሌ 45 ኪሎሜትርን ተጉዞ ትምህርቱን ቀጠለ፣ ነገር ግን 7ኛ ክፍል ሲደርስ መመላለስ የማይቻል ሆነ፣ አባት በ ሞራልም በ ገንዘብም መደገፍ ይችሉ ነበር።
ነገር ግን የሚፈልጉት ልጃቸው ጥሩ ገበሬ እንዲሆን ነበር፣ ልጅ ደግሞ ምንም ህልም በ ውስጡ ሳይኖር የ ሂሳብ እና ፊዚክስ ፍቅሩ ከ አቅም በላይ ጨመረ፣ በዚህም የተነሳ የሚያድርበትም ሆነ የሚመገበው ሳይኖረው እጅ እና እግሩን ብቻ ይዞ 7ኛ ክፍልን ለመማር እዛው ሀረርጌ ውስጥ የምትገኝ ትንሽ ከተማ በሮዳ ሄደ፣ ምግብ እንዲያበሉት እና እንዲያሳድሩት ብቻ በመጠየቅ የ ሰዎችን ልጆች ማስጠናቱን ተያያዘው ፣ በዚህ ሂደት ውስጥ ተነግሮ የማያልቅ ፈተናዎችን መጋፈጥ ነበረበት፣
ከ ላይ የተጻፈው ታሪክ ድርሰት ወይም አፈታሪክ አይደለም፣ የተኖረ ሂወት እንጂ፣ ያውም የ ናሳው ሳይንቲስት ዶ/ር Tilaye Tadesse እውነተኛ ታሪክ ነው ፣ እናም ስለ አጠቃላይ የ ስራው እንቅስቃሴ በሰፊው አስረድቶናል ይከታተሉት፣ የማሩበታል፣ |@yomtech #tilayetadese #ermiasalemayehu #technology #nasa