Перейти к содержимому

የተመረጡ የበአታ ማርያም መዝሙሮች | | beata maryam | | ዘወትር የሚደመጡ የእመቤታችን መዝሙሮች

ሩሃማ ዜማ

0:00 / 0:00

የተመረጡ የበአታ ማርያም መዝሙሮች | | beata maryam | | ዘወትር የሚደመጡ የእመቤታችን መዝሙሮች

22 329 просмотров · 9 мес. назад
ሩሃማ ዜማ
502 подписчика
22 329 просмотров · 9 мес. назад
ንጽሕተ ንጹሐን፣ ቅድስተ ቅዱሳን፣ ከተመረጡ የተመረጠች፣ ከተለዩ የተለየች፣ ከተከበሩ የተከበረች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከእናቷ ከቅድስት ሐናና ከአባቷ ቅዱስ ኢያቄም በእግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ ከተወለደችበት ዕለት ግንቦት ፩ ቀን ጀምሮ በወላጆቿ ቤት ለሦስት ዓመት ከኖረች በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ታኅሣሥ ፫ ቀን ‹‹በዓታ ለማርያም›› በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ ኢያቄምና ሐና የተሳሉትን ስእለታቸው አስታውሰው ወስደው ለቤተ እግዚአብሔር ሲሰጧትም ካህኑ ዘካርያስ ስለምግቧ ተጨነቀ፤ ሕዝቡንም ሰብስቦ ሳለ መልአኩ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ይዞ ከሰማይ ወረደ፤ ዘካርያስ ለእርሱ የመጣ ሀብት መስሎት ታጥቆ እጅ ነሥቶ ቢቆም ወደ ላይ ራቀበት፡፡ ከስምዖን ጀምሮ በዚያ የተሰበሰቡት ሰዎችም በተራ ቢሞክሩ በተመሳሳይ መልኩ ወደ ላይ ራቀባቸው፡፡ ‹‹ምን አልባት ለእንግዶች የመጣ ሀብት እንደሆነ›› ብለው ሐና እና ኢያቄም እንዲቀርቡ አደረጓቸው፤ ነገር ግን ለእነርሱም ራቀባቸው፤ ዘካርያስም ሐናን ‹‹እግዚአብሔር የሚያደርገውን የሚያውቅ የለምና ልጅቷን ትተሸ ወደዚህ ነይ›› አላት፤ በዚያም ጊዜ ቅድስት ማርያም እናቷን ስትከተል መልአኩ ፋኑኤል ወደ እርሷ ቀርቦ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ መገባት፤ ከዚያም በክብር ዐረገ፤ ሊቀ ካህናቱና ሕዝቡም ‹‹የምግቧ ነገር ከተያዘልን በቤት እግዚአብሔር ትኑር›› ብለው ወደ ቤተ መቅደስ አስገቧት፡፡ ለአባ ሕርያቆስ ፤ለቅዱስ ኤፍሬም ፤ለቅዱስ ያሬድ ፤ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የተገለጸች እመቤታችን እኛንም በበረከት እና በረድኤት ትጎብኘን ፤ ለበላኤ ሰብዕ የተለመነች እመ አምላክ ለኛም ትለመነን ከልጅዋ ከወዳጅዋ ከመድኃኔዓለም ዘንድ ታማልደን አሜን ወስብሐት ለእግዚአብሔር !!! ይህ ቪዲዮ ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር፣ ላይክ እና ሰብስክራይብ በማድረግ ያበረታቱን። እግዚአብሔር አብዝቶ ይባርክልን!    • የተመረጡ የበአታ ማርያም መዝሙሮች | | beata maryam | |...   የቅድስት ድንግል ማርያም መዝሙሮች ስብስብ | Ethiopian Orthodox Mezmure| ዘወትር የሚደመጡ|ልደታ|ledeta|በአታ ማርያም|beata maryam    • የኪዳነምህረት መዝሙሮች ስብስብ| kidane miheret Mezmur...   #በአታማርያም#beata maryam#ድንግል_ማርያም,#እመቤታችን_ማርያም,#የእመቤታችን_መዝሙር,#የበአታ_ማርያም_መዝሙር,#ኦርቶዶክስ_መዝሙር_ስብስብ,#አዲስ_ዝማሬ,#Mezmur,#የኦርቶዶክስ_መዝሙር,#MariamMezmur,#ማኅበረ_ቅዱሳን,#ጃንደረባው,#Zemari_Theodros_Yosef,#ኦርቶዶክስ_መዝሙር_ስብስብ #Zemari_Abel_Mekbib,#ዘማሪ ምንዳዬ ብርሃኑ,#mariammezmur #እመቤታችን_ማርያም #እጅግ_አዲስ_የእመቤታችን_መዝሙር,#አዲስ_ዝማሬ_ድንግል_ማርያም_2025,#አዲስ_ዝማሬ_ድንግል_ማርያም_2018,#የበአታ_ማርያም,#BeataMariamMezmur,#የህዳር_ጽዮን_ማርያም_መዝሙር#ኪዳነ_ምህረት#gebrale,maleda mezmure,የማለዳ መዝሙር,#የኤርትራ_ኦርቶዶክስ,ማርያም