እንኳን በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን መልካም በሃል። ሶል ፎቶ
Sol foto
0:00 / 0:00
እንኳን በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን መልካም በሃል። ሶል ፎቶ
84 просмотра · 2 нед. назад
Sol foto
876 подписчиков
84 просмотра · 2 нед. назад
እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላምና በጤና በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!
"ጊዜያትንና ዘመናትን ይለውጣል፤ ነገሥታትን ያፈልሳል፣ ነገሥታትንም ያስነሣል፤ ጥበብን ለጠቢባን፣ ዕውቀትንም ለአስተዋዮች ይሰጣል።" (ዳንኤል 2:21)
በዚህ አዲስ ዓመት አዲስ ተስፋ ይዞልን የሚመጣውን ዘመን ከእግዚአብሔር ጋር የምንጀምርበት፣ ከእርሱም ጋር ይበልጥ የምንቀራረብበት ይሁንልን! ያለ እርሱ ምርጫም ሆነ አማራጭ እስከማይኖረን ድረስ እግዚአብሔርን ብቻ የምንከተልበት ዘመን ይሁን።
በአዲሱ ዓመት እጃችሁ ለመቀበል ሳይሆን ለመስጠት ይዘርጋ፤ እግዚአብሔርም የምትሰጡትን አይንሳችሁ። ይስሐቅ ከእናቱ ሞት በኋላ በርብቃ እንደተጽናና፣ ባለፈው ዓመት ካዘናችሁበት ነገር ሁሉ የምትጽናኑበትን መልካም ነገር እግዚአብሔር ይስጣችሁ።
እግዚአብሔር የእናንተ የሆነውን ነገር ሁሉ ይባርክልዎ፤ የለፋችሁበትንና የደከማችሁበትን ፍሬ የምትቀበሉበት ዓመት ያድርግላችሁ። የማያውቋችሁ አይተው ይውደዷችሁ፤ የሚሰሟችሁም ያክብሯችሁ። ከከንቱ ድካምና ከፍሬ-አልባ ሥራ ይጠብቃችሁ፤ "በቀረብኝ" የማያሰኝ፣ የማትቆጩበትን ሙሉ ደስታ ይስጣችሁ።
ከሁሉ በላይ ደግሞ ለእግዚአብሔር የልብ ሀሳብና ለቅዱስ መንግሥቱ ያብቃችሁ! ያብቃን አሜን አሜን አሜን
ሶል ፎቶ
🌻
🌻 መልካም አዲስ ዓመት! 🌻
መልካም አዲስ አመት🌻🌻🌻🌻🌻