ኢቅላብ አደራረግ አል ኒሳእ ኮድ 2️⃣🔰 የኪታብ እና ቁርአን ✅ መቅረያ መርከዝ
Global University for Women! 🌍📖 النساء
0:00 / 0:00
ኢቅላብ አደራረግ አል ኒሳእ ኮድ 2️⃣🔰 የኪታብ እና ቁርአን ✅ መቅረያ መርከዝ
961 просмотр · 1 год назад
Global University for Women! 🌍📖 النساء
3,08 тыс. подписчиков
961 просмотр · 1 год назад
ኢቅላብ አደራርግ
አል ኒሳእ ኮድ 2️⃣🔰 የኪታብ እና ቁርአን ✅ መቅረያ መርከዝ
🔀 የተጅዊድ ትምህርት ክፍል - አስር🫵🫵🫵🫵🫵🫵🫵🫵🫵🫵🫵🫵🫵🫵🫵
🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜🔜
⭕️ የኑን ሳኪና እና ተንዊን ህግጋቶች
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️🔰〰️〰️〰️〰️〰️〰️🔰〰️🔰〰️
🫵🫵🫵👉👉 ❸) ኢኽፋዕ
⛔️ኢኽፋዕ ማለት በቋንቋ ደረጃ መደበቅ ማለት ሲሆን በተጅዊድ ሊቃውንቶች አገላለፅ ደግሞ ኢኽፋ ማለት ሱኩን የሆነን ፊደል ሸዳ ካለመጠቀም ጋር በኢዝሃር እና በአድጋም መካከል አድርጎ በመጀመሪያው ፊደል (በኑን ሱኩን ወይም ተንዊን) ላይ ጉና በማስገባት ማንበብ ማለት ነው።
🛑 ከ 28ቱ የአረበኛ ፊደላቶች የኢኽፋዕ ፊደል የሚባሉት ⓵⓹ ናቸው።
እነርሱም፦ 👇👇👇👇👇👇
ص ذ ث ك ج ش ق س د ط ز ف ت ض ظ
◆ እነዚህን ፊደላቶች በቀላሉ ለመያዝበ ቀጣዩ ሁለት የግጥም ቤቶች በእያንዳንዳቸው ቃሎች መጀመሪያ መጀመሪያ ላይ ተጠቃለው እናገኛቸዋለን።
صِفْ ذَا ثَنَا كَمْ جِادَ شَخْصٌ قَدْ سَمَا
دُم طَيْبًا زِدْ فِي تُقًى ضَعْ ظَالِمًا
● በአጭሩ ቁርአን በምንቀራበት ጊዜ እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩት 15 ፊደላቶች ከኑን ሱኩን ወይም ከተንዊን በኋላ ከመጡ ኑን ሱኩኑን ወይም ተንዊኑን ጉና በመጠቀም ኢኽፋዕ አድርገን (ደብቀን) እናነባቸዋለን ማለት ነው።
ምሳሌ፦ ሷድ 👇👇👇👇👇👇
➙ ከኑን ሱኩን በኋላ ሷድ (ص) ሲመጣ👇👇👇👇👇👇
●عَن صَلَاتِهِمْ ●وَٱنصُرْنَا ●مِن صَدَقَةٍ
➙ ከተንዊን በኋላ ሷድ (ص) ሲመጣ 👇👇👇👇👇👇
●قَاعًا صَفْصَفًا ●قَوْمًا صَٰلِحِينَ
➦ ለቀሪ ፊደላችም ከቁርአን ብዙ ማምጣት ይቻላል በዚህ መሰረት እናንተ ሞክሩ።
⭕️ የኢድጋም እና የኢኽፋ አንድነት እና ልዩነታቸው
📛 አንድነታቸው
➦ አንድ የሚያደርጋቸው በሁለቱም ጊዜ ጉና እንጠቀማለን።
📛 ልዩነታቸው
➦ በኢድጋም ጊዜ ጉና ስናወጣ ሸዳ ስንጠቀም በኢኽፋዕ ጊዜ ግን ጉና ስናወጣ ሸዳ አንጠቀምም።
➦ ኢኽፋዕ ስናደርግ ጉና የምናወጣው መጀመሪያው ፊደል ላይ ማለትም ኑን ሱኩን ወይም ተንዊን ላይ ሲሆን ኢድጋም ስናደርግ ግን ጉና የምናወጣው ከኑን ሱኩን ወይም ተንዊን ቀጥሎ ከሚመጣው ከአድጋሙ ፊደል ላይ ነው።
➦ በኢኽፋዕ ጊዜ ኑን ሱኩን ከኢኽፋው ፊደል ጋር በአንድ ቃል መምጣት የምትችል ስትሆን በኢድጋም ጊዜ ግን ኑን ሱኩን አድጋም ትሆን ዘንድ ከኢድጋሙ ፊደል ጋር በአንድ ቃል ላይ መምጣት የለባትም።
➦ በኢኽፋ ጊዜ ከኑን ሳኪና ወይም ተንዊን በሗላ አምስት የሚወፍሩ ( ص ض ط ظ ق ) ሲመጡ ጉናውን እናወፍራለን። በኢድጋም ጊዜ ግን ጉና አይወፍርም።
➦ የኢድጋም ፊደላቶችን ኢድጋም ቢጉና እና ቢገይሪ ጉና ተብለው ይከፈላሉ የኢኽፋ ፊደላቶች ግን ሁሉም ጉና አላቸው።
👌👌ማስታወሻ
🛑 ኢኽፋዕ በሁለት ይከፈላል።
1) ኢኽፋዕ ሀቂቂይ፦ ከኑን ሱኩን እና በተንዊን በሗላ የኢኽፋዕ ፊደላቶች በሚመጡበት ጊዜ የሚፈጠር ኢኽፋዕ ነው። በሌላ አገላለፅ የኑን ሱኩን ወይም የተንዊን ኢኽፋ ኢኽፋዕ ሀቂቂይ ተብሎ ይጠራል።
2) ኢኽፋ ሸፈዊይ፦ ከሚም ሱኩን በሗላ የ 'ባ' ፊደል በሙምጣቱ ምክንያት ሚም ሱኩን ኢኽፋ ተደርጋ ትነበባለች። ይህ የሚም ሱኩን ኢኽፋ ኢኽፋ ሸፈዊይ ተብሎ ይጠራል።
👌👌👌❹) ኢቅላብ
⛔️ ኢቅላብ ማለት በቋንቋ ደረጃ አንድን ነገር ገፅታውን መቀየር ወይም መለወጥ ማለት ሲሆን በተጅዊድ ምሁራኖች አገላለፅ ደግሞ ከኑን ሱኩን ወይም ከተንዊን በሗላ የ 'ባ' ፊደል በምጣቱ ምክንያት ኑን ሱኩኑን ወይም ተንዊኑን ወደ ሚም ፊደል በመገልበጥ ጉና ተጠቅመን ማንበብ ማለት ነው።
🛑 ከ 28ቱ የአረበኛ ፊደላቶች ውስጥ የኢቅላብ ፊደል አንድ ብቻ ሲሆን እሱም 'ባ' (ب) ነው።
ምሳሌ፦ 🫵🫵🫵🫵
➙ ከኑን ሱኩን በሗላ የ ባ ፊደል ሲመጣ 👇👇👇👇👇👇
●مِن بَعْدِ
●يُنبِتُ لَكُمْ
➙ ከተንዊን በኋላ የ ባ ፊደል ሲመጣ 👇
●سَمِيعٌ بَصِيرٌ
➦ ቁርአን በምንቀራበት ጊዜ ኢቅላብ መሆኑን በቀላሉ ለመለየት ሁልጊዜ ከኑን ሱኩን ወይም ከተንዊን ከላይ በኩል የተቀመጠች ትንሽ ሚም ፊደል ትመጣለች በዚህ ጊዜ ኢቅላብ መሆኑን እንረዳለን ማለት ነው።
👌👌 ማጠቃለያ
⛔️ በኑን ሱኩን ወይም ተንዊን ህግ ጊዜ 28ቱ የአረበኛ ፊደላቶች ውስጥ 👇
◆ የኢዝሃር ፊደላቶች የሚባሉት ❻ ናቸው።
【 أ ه ع ح غ خ 】👈
◆ የኢድጋም ፊደላቶች የሚባሉት ❻ ናቸው።
【 ي ر م ل و ن 】👈
◆ የኢኽፋዕ ፊደላቶች የሚባሉት ❶❺ ናቸው።
【ص ذ ث ك ج ش ق س
د ط ز ف ت ض ظ】
◆የኢቅላብ ፊደል አንድ ❶ ብቻ ነው።
👌👉【 ب 】👈
➦ በአጠቃላይ የኢዝሃር ❻ + የኢድጋም ❻ + የኢኽፋዕ ❶❺ + የኢቅላብ ❶ = ❷❽ የአረበኛ ፊደላቶች ይሆናሉ።
=============================
=============================
ይቀጥላል............. ኢንሻ አላህ ‼️ሼረ ልለልሎች እንደ ደረሰ
አል ቁርአን ዩኒቨር ሲቲ