“አልፋና ኦሜጋ” (የሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወልደ ቂርቆስ መዝሙር በማኅበረ ቅዱሳን የበገና ዘማርያን)
Mahibere Kidusan
0:00 / 0:00
“አልፋና ኦሜጋ” (የሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ ወልደ ቂርቆስ መዝሙር በማኅበረ ቅዱሳን የበገና ዘማርያን)
45 685 просмотров · 6 л. назад
Mahibere Kidusan
597 тыс. подписчиков
45 685 просмотров · 6 л. назад
አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ
በከሃዲዎች እጅ ተይዘህ ቀረብክ
ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ
እየደበደቡ ክርስቶስ ሆይ አሉህ
ጽድቅን ስለ ሠራህ በወንጀል ከሰሱህ
ለአዳም ቤዛ ብለህ ብዙ ተንገላታህ
አዝ…
ቅዱሳን እጆችህ የፍጥኝ ታስረው
እንደ በግ ተጎተትህ ልትመራቸው
የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ
ፊትህን ሸፈኑህ ለመመጻደቅ
አዝ…
በዓውደ ምኩናን ከጲላጦስ ፊት
አሳልፈው ሰጡህ አጋልጠው ለፍርድ
ከሐና ቀያፋ ከመሳፍንቱ ደጅ
ከነሄሮድስም ዘንድ አቀረቡህ በአዋጅ
አዝ…
ግርፋት ሕማሙ አልበቃ ብሎህ
በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ
ሳዶርና አላዶር ዳናትና አዴራ
ተፈልገው መጡ በችንካር በተራ
አዝ…
የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ
ሊያያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ
ግፈኞች አይሁዶች በአንተ ላይ ቀለዱ
ምራቅን ተፉብህ እራስህን ሊጎዱ