Перейти к содержимому

New Ethiopian Orthodox Mezimur # ከበውናል እንጂ አልጋረዱንም።# በነገረ ቅዱሳን ላይ የተዘመረ አዲስ ዝማሬ # በመልአከ ገነት ዲበኩሉ በላይ

Kesis Dibekulu Belay Official

0:00 / 0:00

New Ethiopian Orthodox Mezimur # ከበውናል እንጂ አልጋረዱንም።# በነገረ ቅዱሳን ላይ የተዘመረ አዲስ ዝማሬ # በመልአከ ገነት ዲበኩሉ በላይ

1 087 просмотров · 6 лет назад
Kesis Dibekulu Belay Official
6,9 тыс. подписчиков
1 087 просмотров · 6 лет назад
በነገረ ቅዱሳን ላይ የተዘመረ አዲስ ዝማሬ ##################### ከበውናል እንጂ አልጋረዱንም፣ ገለጡልን እንጂ አልሸፈኑንም፣ ቅዱሳን በቃል በኑሯቸው፣ የመንግስቱን ወንጌል አነበብንባቸው። እግዚአብሔርን በመምሰል በቅድስና፣ ዓለምን ዞሩ በፍቅር በትሕትና፣ መታሰቢያ ሰጣቸው ለዘለዓለም፣ ተሹመዋል ሊፈርዱ በዓለም። ከወዳጁ ከአብርሃም፣ የሚሠውረው ምንም የለም፣ እግዚአብሔር ስለ ቅዱሳኑ፣ ብዙ ነው ማዳኑ። አዝ... የክርስቶስን ፍቅር በልብ የተሸከሙት፣ ራሳቸውን በመካድ የተከተሉት፣ ቅዱሳን ናቸው የግንዱ ቅርጫፎች፣ የተባሉ የአምላክ ወዳጆች። ከወዳጁ ከአብርሃም፣ የሚሠውረው ምንም የለም፣ ጌታ ስለ ቅዱሳኑ፣ ብዙ ነው ማዳኑ። አዝ... የቅዱሳኑ ጸሎት ኃይልን ያደርጋል፣ ቃል ኪዳናቸው በጽኑ ድንቅን ይሠራል፣ በጻድቁ ስም ጻድቁን የሚቀበል፣ የጻድቁን ዋጋ ያገኛል። ከወዳጁ ከአብርሃም፣ የሚሠውረው ምንም የለም፣ እግዚአብሔር ስለ ቅዱሳኑ፣ ብዙ ነው ማዳኑ። አዝ... እግዚአብሔር ተገልጧል በጻድቁ ላይ፣ አምላክ ተደርጓል በጸጋ በፈርዖን ላይ፣ ይነገራል ገድላቸው በዓለም ሁሉ፣ ድንቆች ናቸው ቅዱሳን በሙሉ። ከወዳጁ ከአብርሃም፣ የሚሠውረው ምንም የለም፣ ጌታ ስለ ቅዱሳኑ፣ ብዙ ነው ማዳኑ።