Перейти к содержимому

መልክዐ እና ታሪክ የአቡነ አቢብ

tsegaselassie shewaamare

0:00 / 0:00

መልክዐ እና ታሪክ የአቡነ አቢብ

129 просмотров · 2 дн. назад
tsegaselassie shewaamare
1,14 тыс. подписчиков
129 просмотров · 2 дн. назад
አቡነ ዕብሎይ፡- ‹‹የመላእክት አምሳል›› የሆነ አባ እብሎይ ከላይ ገድላቸውን ያየነው የአቡነ አቢብ የቅርብ ጓደኛቸው ነው፡፡ የአቡነ እብሎይ አባቱ አሞኒ እናቱ ሙስያ ይባላሉ፡፡ ሁለቱም በእግዚአብሔር ፊት ቅዱሳን ነበሩ፡፡ በሕጉ ጸንተው የሚኖሩ መጻተኞችንና ድኆችን የሚረዱ ናቸው ነገር ግን ልጅ አልነበራቸው፡፡ ከዕለታትም በአንደኛው ቀን ቅድስት ሙስያ እንጨት የያዘ ብርሃናዊ ሰው በቤቷ ውስጥ ሲተክለውና ወዲያውኑ ለምልሞ አብቦ ሲያፈራ ያ ብርሃናዊ ሰውም ‹ከዚህ ፍሬ የሚበላ ሁሉ ለዘለዓለም ይኖራል› ሲላት እርሷም ከፍሬው ወስዳ ስትበላና በአፏ ውስጥ ጣፋጭ ሲሆንላት በልቧም የልጅ ፍሬ ይሆንልኝ ይሆን ሰትል አሰበች፡፡ በነቃችም ጊዜ ለባሏ ያየችውን ስትነግረው እርሱም ይህንኑ ራእይ እንዳየ ነገራት፡፡ ሁለቱም እግዚአብሔርን ካመሰገኑ በኋላ ተጋድሎቸአውን ከፊት ይልቅ ጨመሩ፡፡ ቅድስት መስያ እብሎይን በፀነሰችው ጊዜ በገድል ወነዶችን እስከምትበልጣቸው ድረስ የምትጋደል ሆነች፡፡ በየሌሊቱ ሁሉ አንድ ሺህ ስግደትን ትሰግድና ብዙ ጸሎትችን ትጸልይ ነበር፡፡ ቀን ሲሆን ደግሞ 500 ስግደትን ትሰግዳለች፡፡ ሕፃኑን እስከወለደችው ጊዜ ድረስ ዘጠኝ ወር ያህል እንዲህ ስትጋደል ኖረች፡፡ ሕፃኑም በተወለደ ጊዜ እብሎይ ብለው ስም አወጡለት፡፡ እብሎይም ከልጅነቱ ጀምሮ ይመነኩስ ዘንድ ይመኝ ነበርና በጎለመሰ ጊዜ አንድ ሌሊት አቡነ አቢብ መጥተው ወሰዱት በላዕላይ ግብጽ ከሚገኙት ገዳማት ወደ አንዱ ወሰዱት፡፡ በዚያም በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመረ፡፡ ከጥቂት ወራትም በኋላ ጥቅምት 25 ቀን አቡነ አቢብ ዐረፈ፡፡ ያንጊዜም አቡነ እብሎይ አብሎግ ወደሚባለው ገዳም ሄደ፡፡ ወደ እርሱም ብዙ ሰዎች መጥተው እየመነኮሱ ተከታዮቹ ሆኑ፡፡ አቡነ አቢብ ካረፉ በኋላ መታሰቢያውን ያደርጉ ነበር፡፡ ማኅበርተኞቹም በጻድቁ በዕረፍታቸው ቀን መታሰቢያቸውን ሲያደርጉ አቡነ እብሎይ እንዲህ አላቸው፡- ‹‹ወንድሞች ሆይ! በአቡነ አቢብ ስም ዛሬ ጸሎት የሚጸልየውን ሰው ኃጢአቱን እግዚአብሔር ያስተሠርይለታል፤ በዕረፍትህ መታሰቢያ ቀን ‹‹የአባ አቢብ ፈጣሪ ሆይ! ኃጢአቴን ሁሉ ተውልኝ› ብሎ አንዲት ጸሎትን የጸለየውን ሁሉ እኔ ኃጢአቱን እተውለታለሁ› ሲል አምላካችን እግዚአብሔር ቃልኪዳን ሰጥቶታልና›› አላቸው፡፡ በዚያችም ሰዓት ከመነኮሳት አንዱ ዐረፈ፡፡ እነርሱም ሊገንዙት በዚያ ቆመው ሳሉ አቡነ እብሎይ ስለ አቡነ አቢብ ቃልኪዳን የተናገረውን ነገር ቃል ከመነኮሳት አንዱ ተጠራጠረ፡፡ በዚያን ጊዜ ያ የሞተው አፈፍ ብሎ ከሞት ተነሥቶ ይናገር ዘንድ ጀመረ፡፡ ‹‹አባ እብሎይ ስለተናገረው ቃልኪዳን ለምን ትጠራጠራላችሁ? ለአባታችን አቢብ በመታሰቢያው ቀን በዚህ ቃልኪዳን እግዚአብሔር ምሕረት ሰጥቶናልና›› አላቸው፡፡ ይህንንም ብሎ ተመልሶ ዐረፈ፡፡ መነኮሳቱም ይህንን በሰሙ ጊዜ እያደነቁ በባሕርይው ምስጉን የሆነውን እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡ አቡነ እብሎይም ከታላቅ ተጋድሎ ብዙ ዘመን ኖረ፡፡ ልጆቹ መነኮሳትም በጣም በዙና በተለያየ ቦታ ገዳማትን ሠሩለት፡፡ እርሱም የኖረበት ዘመን ታላቁ አባ መቃርስ በነበረበት ዘመን ነውና ታላቁ አባ መቃርስ የአባ እብሎይን ምግባር ሃይማኖቱን፣ ዜና ትሩፋቱን፣ ጽኑ ተጋድሎውን በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ ተሰኘበት፡፡ እርሱንም ሆነ መነኮሳት ልጆቹን የምታረጋጋና የምታጽናና ግሩም የሆነች መልዕክትን ጻፈለት፡፡ ይህንንም አባ መቃርስ በአስቄጥስ ገዳም ሆኖ ሲጽፍ አባ እብሎይ ደግሞ በላዕላይ ግብፅ ሳለ መንፈስ ቅዱስ ዐውቆ በዙሪያው ያሉትን መነኮሳት ልጆቹን ‹‹እነሆ ማጽናናትን የተመላች መልዕክት አባታችን መቃርስ ጻፈልን›› አላቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ከአባ መቃርስ ዘንድ የተላኩት መነኮሳት ወደ እነርሱ ሲመጡ ጠብቀው በታላቅ ደስታ ተቀበሏቸው፡፡ የአባ መቃርስንም መልአክት ለአባ እብሎይ ሰጡትና እርሱም በመነኮሳቱ ሁሉ ፊት አነበባት፡፡ ሁሉም በመልእክቷ እጅግ ደስ ተሰኙ፡፡ ከዚህም በኋላ አቡነ እብሎይ ከዚህ ዓለም ድካም የሚያርፍበት ጊዜ ሲደርስ ተገልጦለት ቃልኪዳን ከሰጠው በኋላ በየካቲት ወር በ5ኛው ቀን በሰላም ዐረፈ፡፡ ነገር ግን የአቡነ እብሎይን ዜና ከወዳጁ ከአቡነ አቢብ ጋር አንድ ላይ መጻፍ ተገቢ ነውና ዕለተ ዕረፍቱ በጥቅምት 25 ቀን አብሮ ይታሰባል፡፡ የአባ እብሎይ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!