Перейти к содержимому

Ethiopian Wot Recipe ቋንጣ ወጥ

Melegna | መለኛ

0:00 / 0:00

Ethiopian Wot Recipe ቋንጣ ወጥ

10 235 просмотров · 1 г. назад
Melegna | መለኛ
190 тыс. подписчиков
10 235 просмотров · 1 г. назад
ቋንጣ ወጡን ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉ ግብዓቶች መጠን እና አይነት ቋንጣውን ለማዘጋጀት 300 ግራም ቀይ ስጋ ቋንጣውን ለመቀመም በቡና ማንኪያ ልኬት 1 የነጭ ሽንኩርት ዱቄት ግማሽ ቁንዶ በርበሬ 1 ጨው 2 ሚጥሚጣ 1 የሾርባ ማንኪያ የተነጠረ ቂቤ የበሶ ብላ እና የሮዝሜሪ ቅጠል 4 የሾርባ ማንኪያ ዘይት የቋንጣ አበሳሰል በቅመሙ በደንብ ለውሳችሁ በላስቲክ ሸፍናችሁ ቢያንስ ለ 1 ሰዓት ማቀዝቀዣ ውስጥ ማስቀመጥ የመጋገሪያ ምድጃ ውስጥ በ150 ዲግሪ የላይኛውንም የታችኛውንም አብርታችሁ ለ 2 ሰዓት ያህል ትጠብሱታላችሁ ፤ ሁሉም ቤት የሚገኘው የምድጃ አይነት እንዲሁም የኤሌክትሪክ መጠን ሊለያይ ስለሚችል ምድጃውን ከፍታችሁ መብሰል አለመብሰሉን ማየት ይኖርባቹሃል ቄሌቱን ለማዘጋጀት 4 ራስ ቀይ ሽንኩርት ግማሽ ብርጭቆ ውሃ ሽነኩርቱን በእንፋሎት ለማብሰል 2 የሾርባ ማንኪያ ዘይት 1 የሾርባ ማንኪያ በርበሬ (የበለጠ ቀላ እንዲል ከፈለጋችሁ የምትጨምሩትን የበርበሬ መጠን ከፍ ማድረግ ትችላላችሁ) 1 የሾርባ ማንኪያ በስል ቂቤ ግማሽ የቡና ማንኪያ የማቁላያ ቅመም 6 ፍሬ ደቆ የተከተፈ ነጭ ሽንኩርት ግማሽ የቡና ማንኪያ ኮረሪማ ውሃ ቁሌቱን ለመከለስ የምትፈልጉትን ያህል ጨው የበሶ ብላ ቅጠል ትንሽ የመከለሻ ቅመም ማባያ እንጀራ