ከውርጃ በኋላ በድጋሜ ለማርገዝ ምን ያህል ጊዜ ያስጠብቃል ?
ጤና Cure
0:00 / 0:00
ከውርጃ በኋላ በድጋሜ ለማርገዝ ምን ያህል ጊዜ ያስጠብቃል ?
18 837 просмотров · 3 г. назад
ጤና Cure
202 тыс. подписчиков
18 837 просмотров · 3 г. назад
ፅንስ ከወረደ ከ2 ሳምንታት በኋላ ኦቭዩሽን ሊከሰት ይችላል። ይህ ማለት አንዲት ሴት ከሚቀጥለው የወር አበባዋ በፊት እንደገና ማርገዝ ትችላለች ማለት ነው።
ፅንሱ ከወረደ በኋላ የወር አበባ ዑደት እንደገና ይጀምራል። ይህ ማለት ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ኦቭዩሌሽን ይካሄዳል ማለት ነው።
በሌላ አነጋገር፣ ከሂደቱ ጥቂት ሳምንታት በኋላ ግንኙነት ካደረጋችሁ፣ ምንም እንኳን የወር አበባ ባታዩም በphysical ደረጃ ሲታይ ልታረግዙ ትችላላቸሁ ማለት ነው።
ሆኖም ግን, ሁሉም ሴቶች የ 28 ቀን ዑደት የላቸውም።, ስለዚህ እርግዝናው የሚፈጠርበት ትክክለኛው ጊዜ ሊለያይ ይችላል። አንዳንድ ሴቶች በተፈጥሮ አጭር የወር አበባ ዑደት አላቸው። ይህ ማለት ከሂደቱ በኋላ በስምንት ቀናት ውስጥ እንቁላል መልቀቅ ሊጀምሩ ይችላሉ እና ብዙም ሳይቆዩ ማርገዝ ይችላሉ።
ሌላው ተጽእኖ የሚያሳድረው ፅንስ ከመውረዱ በፊት ያለው የእርግዝና ጊዜ ነው። ኦቭዩሌት የማድረጉ ሁኔታም እርግዝናው ከመውረዱ በፊት ምን ያህል እርዝማኔ ላይ እንደነበረ ይወሰናል። የእርግዝና ሆርሞኖች ከሂደቱ በኋላ ለጥቂት ሳምንታት በሰውነታችሁ ውስጥ ሊቆዩ ይችላሉ።ይህ መሆኑ ኦቭዩሽን እና የወር አበባ መዘግየትን ያመጣል።
#pregnancy
#healthy
#ውርጃ