Перейти к содержимому

👉 መስከረም 07#የቅድስት ኤልሳቤጥ የእረፍት ቀን

Kerbe tube

0:00 / 0:00

👉 መስከረም 07#የቅድስት ኤልሳቤጥ የእረፍት ቀን

21 просмотр · 12 дней назад
Kerbe tube
592 подписчика
21 просмотр · 12 дней назад
« አ ሁ ን ፡ አ ረ ፈ ች ፡ እ ህ ት ሽ ፡ ኤ ል ሳ ቤ ጥ » #መስከረም_ሰባት_ቀን_ቅድስት_ኤልሳቤጥ_ዐረፈች ቅድስት ኤልሳቤጥ የቅዱስ ዮሐንስ እናት የጽድቅ እመቤት ከመሆኗም በላይ የቅድስት ድንግል ማርያም የቅርብ ዘመድ በትሕትናዋ የምትወደድ ደገኛ ሴት ናት ። ሰውነቷ ከኀጢአት ንግግሯ ከትዕቢትና ከስሕተት የታረመ በመንፈስ ቅዱስ የተቀመመ ከቅዱስ ገብርኤል ቀጥላ ስለወላዲተ አምላክ ስለ ድንግል ማርያም ማንነት የመሰከረች በዘመኑ ለነበሩ ማኅበረሰብ ወንጌልን የሰበከች የመጀመሪያዋ የሴት ሐዋርያ የሆነች ክብርት ሴት ናት ቅድስት ኤልሳቤጥ ። በዝምድና አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የእናቷ እኅት ልጅ ናት ይችንም ቅድስት ኤልሳቤጥ ካህኑ ዘካርያስ አገባት የከበረ ወንጌልም ኹለቱም ያለ ነውር ያለ ነቀፋ በእግዚአብሔር ሕግ ጸንተው የሚኖሩ እውነተኞችና ጻድቃን ሆነው እንደኖሩ መስክሮላቸዋል ። ኤልሳቤጥ መካን ስለሆነች ወደ እግዚአብሔር የሚለምኑና የሚማልዱ ሆኑ አርጅተውም የመውለጃቸው ዘመን ባለፈ ጊዜ እግዚአብሔር መልአኩን ገብርኤልን ወደ ዘካርያስ ልኮ ልመናቸው እንደ ተሰማና ዮሐንስን እንደሚወልዱ አበሠረው ። ከዚህም በኋላ ቅድስት ኤልሳቤጥ መጥምቁን ዮሐንስን ፀንሳ ወለደች ከሰዎችም የሚደርስባት ሽሙጥ ተወግዶ እጅግ ደስ አላት ሕፃኑም በማሕፀኗ እያለ እመቤታችን ድንግል ማርያም ሰላምታ በሰጠቻት ጊዜ እንዲህ ብላ ጮኸች ፦ « አንቺ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሸ የተባረክሽ ነሽ የማኅፀንሽም ፍሬ ቡሩክ ነው የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እኔ ምንድን ነኝ እነሆ እንዴት ነሽ ስትይኝ የሰላምታሽን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ልጁ በማኅፀኔ ውስጥ በደስታ ዘለለ»ብላ የእመቤታችንን ወላዲተ አምላክነትን መሰከረች ። ከዚህም በኋላ ጌታችንን አየችው በአምላክነቱም አመነች የሚያምኑበት በመዳናቸው ደስ አላት ስትል መስክራለች ኤልሳቤጥ ልጅዋን ዮሐንስን ከሄሮድስ ሰይፍ ለማሸሽ በስደት በሐቅለ ዮሳፍጥ እንዳለች ከዚህ ዓለም #መስከረም_ሰባት_ቀን_ዐርፋለች። እመቤታችን ተወዳጅ ልጇን አዝላ አረጋዊ ዮሴፍና ሰሎሜን አስከትላ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በስደት ኖራ ከኢትዮጵያ ተነሥታ በመስከረም ወር ግብፅ ገባች ፤ በሐቅለ ዮሳፍጥ አቋርጠው ሲሄዱ ሕፃኑ ኢየሱስ ክርስቶስ #አሁን_አረፈች_እህትሽ_ኤልሳቤጥ እያለ በሕፃን አንደበቱ እየደጋገመ ቅድስት ኤልሳቤጥ ወዳረፈችበት ቦታ በጣቱ እየጠቆመ ያሳያቸው ጀመር ። እነርሱም ወደ ጠቆማቸው ቦታ ቢሄዱ ቅድስት ኤልሳቤጥ አርፋ ልጇ ዮሐንስ ሙት የሆነውን የእናቱን ጡት ሲገጠግጥ አገኙት ፤ ዮሐንስ ሰው አይቶ ስለማያውቅ ምን መጣብኝ ብሎ ደንግጦ ከዱር ገባ ፤ እመቤታችን አረጋዊ ዮሴፍና ሰሎሜ አልቅሰው መቃብሩን የታዘዘ አንበሳ መጥቶ ቆፍሮላቸው በዚያ በዮሳፍጥ በረሃ አጥበው ገንዘው ቀብረዋት ሔደዋል ። እመቤታችን አረጋዊ ዮሴፍን ዮሐንስን አባብለው ከተደበቀበት ዱር ጫካ እንዲያመጣው ልትልከው ስትል ሕፃኑ ክርስቶስ « ተውት እሺ አይላችሁም ጊዜው አልደረሰም ሠላሳ ዘመን ሲሞላው እርሱ ራሱ በክብር ይገለጣል ከፊቴ እየቀደመ የንስሐ ትምህርትን እያስተማረ መንገዴን የሚጠርገው እርሱ ነው » አላቸው ከዚያም ትተውት ሔደዋል ። ዮሐንስም ሠላሳ ዘመን እስኪሞላው ድረስ በዚያው በተሰደደበት በረሃ አድጓል ኤልሳቤጥ የቅድስት ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክነትን በማብሠር የመጀመሪያ ሴት ሐዋርያዊት ስትሆን ልጇ ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነትን በማብሠር የመጀመሪያ ሐዋርያ ሆኗል ። በዚህም እናትና ልጅ በተመሳሳይ ሰዓት ተመሳሳይ ምስክርነትን በመስጠት ከመላእክት ቀጥሎ ከሰው ዘር አስቀድሞ የሥጋዌን ምሥጢር ገበታ በመቅመስ የመጀመሪያና ብቸኛ ናቸው ። ቅዱስ ያሬድ የእናትና የልጅን ሕይወት እንዲሁም የሰጡትን ምስክርነት በድጓው እንዲህ ሲል ዘምሮላቸዋል « ኤልሳቤጥ ማርያምን ቃልሽን በሰማሁ ጊዜ በማኅፀኔ ያለው ልጅ በደስታ ዘለለ አንቺ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሸ የተባረክሽ ነሽ አለቻት መልአኩም ኤልሳቤጥን ተናገራት የዮሐንስን እናት እንዲህ አላት ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ የሚያሰክር ወይንና ጠጅን አይጠጣም መንፈስ ቅዱስ በላዩ ላይ ያድርበታል ( ይመላበታል ) የሙሽራው ወዳጅ ይባላል » በማለት ቅድስት ኤልሳቤጥ የወለደችው የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነ ጻድቅና ነቢይ መሆኑን በድጓው ዘምሯል ።