Перейти к содержимому

ቢኖሩ - Binoru ﷺ • አዲስ የህብረት ነሺዳ • Liqa #2 ሊቃእ መድረክ#2

ABDU ABERA

0:00 / 0:00

ቢኖሩ - Binoru ﷺ • አዲስ የህብረት ነሺዳ • Liqa #2 ሊቃእ መድረክ#2

1 089 443 просмотра · 4 г. назад
ABDU ABERA
119 тыс. подписчиков
1 089 443 просмотра · 4 г. назад
#mezamir #abduselam #liqa #neshida #nasheed #ethiopia #muslim ሊቃእ መድረክ #2 ላይ የቀረበ የህብረት ነሺዳ ሙንሺዶች ዓብዱሰላም ሰዕድ አህመድ ፈይሰል ሰመር አቡበከር ሰፊዩ ግጥም መሀመድ ኢድሪስ ካሳ ዜማ ዓብዱሰላም ቅንብር ኤሉና ስቱድዮ ቪዲዮ ሚንዛር ፕሮዳክሽን ----------------------------- የነሺዳው ግጥም ቢኖሩ ኖሮ የኣለሙ ጀማል መቼ የምድሩ ሚዛን ይዘማል ሀቀኛ ወድቆ ፋሲቅ ይሾማል መቼ እንደሀላል ፈሳድ ይዜማል ። ላልቶ ከስሩ የዋህዳው ኪዳን ነገድ ሲያዋድድ ሀረግ ሲያካዳን ውሉ ሲጠፋ . . . የዘመን መልኩ ጠልሽቶ ሲቀር ምን ኣለ መላ ኣንቱ ብትኖሩ ከማለት በቀር ። ቢኖሩ ኖሮ ሐቅ ኣይቀበር ኢልም ተንቆ ጀህል ኣይከበር ቢኖሩ ዘይኔ የከውኑ ኣለቃው በሒክማቸው ቃል በረጋ ሊቃው ። ቢኖሩ ኖሮ ሰይደል ዑመም ፍትህ ኣይቆስል ሓቅ ኣይታመም ጥላቻ ኣይሾም ህብረት ተሽሮ እዝነት ኣይሞትም ቂም ተሞሽሮ ። ቢኖሩ ኖሮ የከውኑ ጀንበር መቼ ይገዝፋል የበደል ቀንበር መቼ ይደምቃል የበላው ኸበር ። ኸልቁን የፍትህ ቀለብ ሲርበው በረካው ሲሸሽ በላ ሲቀርበው ሲዛነፍ ለዛው የመኖር ጣሙ ኣንቱ በኖሩ በረጋ ኣለሙ ። ኸይር ሲኮስስ ዙልም ፈንድቆ መሃባ ሲነጥፍ ቂም በቀል ደምቆ ፍጥረት ሲዛነፍ ልኩ መስመሩ እንዴት ኣያሰኝ ምነው በኖሩ ። ሙስሊም ከሙስሊም ወንድም ከወንድም ውሉ ሲላላ ፍቅሩ ሲወድም ዋህዳው ሲበተን ከልቡ ሾልኮ ምነው በኖሩ ያሰኛል እኮ ። ስንጨካከን ጥርስ ተናክሰን ጎራ ተቧድነን ሰርክ ተካሰን ሜዳ ሲወጣ ነውራችን ደምቆ ማለቀስ ነው'ንጂ ጀማሌን ናፍቆ ኣንቱ ብትኖሩኝ ያበድረል ከማል የነፍሴ ኪዳን በሱናሁ ቢማል ሸክሌ ባማረ የቀልቤ ጀማል ። ቢኖሩ እያልኩ መብሰክሰኬማ ልቤ ሱናሁን ደርሶ ቢጠማ ናፍቆት ኣስሮኛል ይዞ በጠና ህያው መኾኔ ባንቱ ነውና ። ምነው በኖሩ ዘይነል ኣለሚን የሓረሙ ሹም ሙስጠፈል ኣሚን