New Gospel song| Singer Shumi Elias| ዘማሪ ሹሚ ኤልያስ| Apostolic Church song| Christian songs
Iso Yisehak Ab
0:00 / 0:00
New Gospel song| Singer Shumi Elias| ዘማሪ ሹሚ ኤልያስ| Apostolic Church song| Christian songs
300 326 просмотров · 4 года назад
Iso Yisehak Ab
35,8 тыс. подписчиков
300 326 просмотров · 4 года назад
የሀዋሳ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን የ7ኛ ካምፕ አጥቢያ ዘማሪ
ግጥም|Lyrics
እግዚአብሔር እኔን ወድዶኛል
የዘላለም ሕይወት ሰጥቶኛል
ኃያላን ጠቢባን ሞልተው
መውደዱ በእኔ ላይ በልጦ
ሳይኖረኝ ምንም ባዶ
እንዲሁ መረጠኝ ወድዶ
ሕይወቴ ዳነና ፀንቶ
ያኑራት አሁንም ገዝቶ
ያዳነኝ/2x/ ኢየሱስ ነው
ሳልገባው የወደደኝ
አይደለም ስላለኝ ብርታት
አሁንም ሕይወቴን ይውሰዳት
1. ሲያከብረኝ ሲወድደኝ ሲለየኝ ከሁሉ
ምን አለኝ የሚያቆመኝ ለክብሩ
እይታው በእኔ ላይ ምንኛ መልካም ነው
ቢኖሩ በዕውቀት ብዙ
ተመረጥኩ በእርሱ እንዲሁ እንዲሁ
ተሰጥቶኛል ስጦታው በነፃ
ቀልሎ አይታየኝ ተከፍሎ የመጣው
ልይዘው ከምንም አምልጬ
እንዳልጠፋ ደምህን ረግጬ
2. ተገብቶኝ አይደለም ሲሰጠኝ አብልጦ
ድኛለሁ ዋጋ ተከፍሎ
መዳኔ ከምንም ከምንም ይበልጣል
ከእጄ ወጥቶ የጠፋ ለታ
ወድቃለሁና አጽናኝ የእኔ ጌታ
እንድገኝ ሠማይ ከአንተ ጋር
ልሸጋገር የምድሩን በኃይልህ
ያስኪደኝ ጠባቡን መንገድ
ታክሎበት የአንተ መወደድ
ያዳነኝ...
3. አበርታኝ አግዘኝ ደግፈኝ ኢየሱስ ሆይ
ድካም አለና በእዚህ በዓለም ኑሮ
ይዤ ይዤ መዳኔን ፅናቱ ሳይኖረኝ
ውድቀቴ ፊትህ እንዳይታይ
እባክህ አፅናኝ እስከሠማይ
እጄን በእጅህ ሳትለቅቅ ይዘኸኝ
ተስፋዬን በዓይኔ አሳይተኸኝ
ዘምራለሁ እላይ በሀገሬ
እያከበርኩ አንተን በዝማሬ
ያዳነኝ...