🔴አዲስ ዝማሬ “እያየህልኝ ነው” ዘማሪ ኢንጂነር ታዴዎስ አውግቸው || (#ዘማሪ_ዲን_አቤል_መክብብ) 📍Official Video 4K
Rama Media ራማ ሚዲያ и ещё 3
0:00 / 0:00
🔴አዲስ ዝማሬ “እያየህልኝ ነው” ዘማሪ ኢንጂነር ታዴዎስ አውግቸው || (#ዘማሪ_ዲን_አቤል_መክብብ) 📍Official Video 4K
5 432 просмотра · 21 ч назад
Rama Media ራማ ሚዲያ и ещё 3
5 432 просмотра · 21 ч назад
እያየህልኝ ነው ያልታየኝን እኔ
እየከለልከኝ ነው ለካስ ሆነህ ጎኔ
እኔ ከማላውቀው ከተሰወረብኝ
መድኃኔዓለም ነህ የምትጠብቀኝ
በጣፋጭ መካከል ያለውን መራራ
የተደበቀን መርዝ ከገበታ ጋራ
ከሳቅ ጀርባ ካለ ከወዳጅ ጥላቻ
አይተህ የምትሰውር አዳኝ አንተ ብቻ
መድኃኔዓለም ሰው በራስ ትንታ
መድኃኔዓለም በሚያልፍበት ዘመን
መድኃኔዓለም ተጠንቅቀህ ሳስተህ
መድኃኔዓለም ታኖራለህ እኔን
ጥያቄዬን ሁሉ ብትፈጽመው ኖሮ
አትንሳኝ ያልኩህን ብትስጠኝ ኖሮ
ዛሬ ሰው ባልሆንኩኝ ቆሜ ባልሄድኩኝ
መንገድ ባትዘጋብኝ እጄን ባትይዘኝ
መድኃኔዓለም በመንሳትም ቸር ነህ
መድኃኔዓለም በመከልከል ቸር
መድኃኔዓለም በኑሮ አስተማሪ
መድኃኔዓለም ደግ መምህር
በራሴ ስከፋ ጠላት ስሆን ለኔ
ንቀህ አልተውከኝም አልጨከንክም በኔ
መንገድ የጠፋኝ ለት ያበራህ በፊቴ
የክፉ ቀኔ ነህ የሌሊት መብራቴ
መድኃኔዓለም እንባ ብቻ ሆንኩኝ
መድኃኔዓለም ሳስብ ያንተን ነገር
መድኃኔዓለም ሳይገባኝ ሳላውቀው
መድኃኔዓለም ለካስ ሞቼ ነበር
የለህም ወይ እያልኩ ያለቀስኩበት ቀን
የስህተት ስህተት ነው ማማረሬ አንተን
ሽንቁሩ ጉደለቴን አተኩሬ ሳየው
ጣትህ ግን የያዘኝ ከገደሉ ላይ ነው
መድኃኔዓለም ከእኔ በላይ ለኔ
መድኃኔዓለም አለልኝ የምልህ
መድኃኔዓለም ከእስትንፋሴም በላይ
መድኃኔዓለም አንተ የቅርቤ ነህ
እያየህልኝ ነው
ዘማሪ ኢንጂነር ታዴዎስ አውግቸው
ድምጽ አጃቢ
ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
ግጥም :-ዘማሪ ኢንጂነር ታዴዎስ አውግቸው
ዜማ:-ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ
Recording, Mixing and Mastering
ዘጎላ ሬኮርድስ
ክራር:- ዘማሪ ዲ/ን ዘላለም ታከለ
መሰንቶ:- አቤል ጥጋቡ
ዋሽንት:- ዘውዱ ንጉሤ
#mezmur #orthodox #mahtot