“አሜሪካ ለፍልስጤም እውቅና ትሰጣለች” እስራኤልን ያናወጠው ቃለ - መጠይቅ! | The US will Recognize Palestine!
GEBEYA GLOBAL
0:00 / 0:00
“አሜሪካ ለፍልስጤም እውቅና ትሰጣለች” እስራኤልን ያናወጠው ቃለ - መጠይቅ! | The US will Recognize Palestine!
2 565 просмотров · 6 ч назад
GEBEYA GLOBAL
129 тыс. подписчиков
2 565 просмотров · 6 ч назад
በእስራኤል ፖለቲካ ውስጥ በተለያዩ ከፍተኛ የኃላፊነት መደቦች ላይ ማለትም የመከላከያ ሚኒስትር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ያገለገሉት፣ Yisrael Beytenu - «እስራኤል ቤታችን» የተባለው ቀኝ-ዘመም (Right-wing) የፖለቲካ ፓርቲ መሪ እና የሀገሪቱ የረጅም ጊዜ ፓርላማ (ክኔሴት) አባል የሆኑት አቪግዶር ሊበርማን አሜሪካ በሁለት ዓመት ውስጥ ማለትም የዶናልድ ትራምፕ የፕሬዝዳንትነት ዘመን ሲያበቃ የፍልስጤምን መንግሥት ልትቀበልና ይፋዊ እውቅና ልትሰጥ እንደምትችል፤ እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) ሙሉ አባል እንድትሆን ውሳኔ እንዲሰጥ ታደርጋለች ሲሉ ገልጸዋል። ሊበርማን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ይህንን ሂደት የሚያውቁት ከመሆኑም በላይ ድርጊቱን ለመግታት ተግባራዊ እርምጃ ባለመውሰድ እያፋጠኑት ነው ብለዋል። ኔታንያሁ ሥልጣን ላይ እስከሌሉ ድረስ አገሪቱ ብትቃጠልም አይገዳቸውም ሲሉም ከባድ ወቀሳ አቅርበውባቸዋል።
እንደ ሊበርማን ገለጻ፣ የሚመሠረተው የፍልስጤም መንግሥት ይሁዳንና ሰማሪያን (ዌስት ባንክ)፣ የዮርዳኖስ ሸለቆን፣ ጋዛን እና ምስራቅ እየሩሳሌምን የሚያካትት በመሆኑ ወደፊት ለመቀልበስ በጣም አስቸጋሪ ይሆናል ብሏል።
ሊበርማን የኦስሎ ስምምነት እንዲሰረዝ እና የፍልስጤም ባለስልጣን (PA) እንዲፈርስ ይሞግታሉ። በዌስት ባንክ ያሉ ፍልስጤማውያንን የዕለት ተዕለት አስተዳደርና የሕዝብ ጸጥታ ኃላፊነት ለዮርዳኖስ በመስጠት፣ እስራኤል ግን የደህንነትና የመሬት ቁጥጥሯን እንድትጠብቅ ሀሳብ ያላቸው ፖለቲካኛም ናቸው። በዝርዝር የምንመለከተው ይሆናል አብራችሁን ቆዩ!
Avigdor Lieberman—leader of the right-wing Yisrael Beiteinu ("Israel Our Home") political party, long-serving Knesset member, and a figure who has held multiple top positions in Israeli politics including Minister of Defense, Minister of Foreign Affairs, and Deputy Prime Minister—stated that the United States could recognize and officially accept a Palestinian state within two years, by the end of Donald Trump's presidential term, and move to grant it full membership in the United Nations. Lieberman asserted that Prime Minister Benjamin Netanyahu is fully aware of this process and is actually accelerating it by failing to take practical measures to halt it. He heavily criticized Netanyahu, claiming the Prime Minister does not care if the country burns down as long as he remains in power.
According to Lieberman, the proposed Palestinian state would encompass Judea and Samaria (the West Bank), the Jordan Valley, Gaza, and East Jerusalem, making it extremely difficult to reverse in the future. Lieberman advocates for canceling the Oslo Accords and dismantling the Palestinian Authority (PA). He is a politician who proposes transferring the daily administration and public security responsibilities over West Bank Palestinians to Jordan, while Israel maintains its overall security and territorial control. We will look into the details—stay tuned and stay with us!
#GebeyaGlobal #GlobalSpecialProgram #GlobalPodcast #GlobalNews #Israel #AvigdorLieberman #Netanyahu #Palestine #WestBank #MiddleEastNews #BreakingNews #USForeignPolicy #Gaza #InternationalRelations