Перейти к содержимому

የእርግዝና 3ተኛው ሳምንት ምልክቶች | The sign of 3rd week pregnancy

ጤና Cure

0:00 / 0:00

የእርግዝና 3ተኛው ሳምንት ምልክቶች | The sign of 3rd week pregnancy

100 276 просмотров · 3 г. назад
ጤና Cure
202 тыс. подписчиков
100 276 просмотров · 3 г. назад
በ3ተኛው የእርግዝና ሳምንት ውስጥ ፅንሰት ተካሄዷል። ይህ ማለት አሁን ነፍሰ ጡር ናችሁ ማለት ነው። ነገር ግን እናንተ አሁንም እንደፀነሳችሁ ላታውቁት ትችላላችሁ። በዚህ ጊዜ የተፈጠረው ፅንስ Morula ይባላል። ታድያ ቀጥሎ ምን ይከሰታል ? 📌ከፅንሰት ቀጥሎ የሚከሰተው መትከል ነው። morula ወደ blastocyts እስኪደርስ ድረስ መከፋፈሉን ይቀጥላል። blastocyts በሚሆንበት ጊዜ ከ 5 እስከ 8 ባሉት ቀናት ውስጥ ማህፀናችሁ ላይ ሄዶ ይጣበቃል። በዚህ ጊዜ ትንሽ ነጠብጣብ የደም ፍሰት ሊገጥማችሁ ይችላል። ይህም ምክንያቱ ፅንሱ በማህፀናችሁ ሲጣበቅ ነው። ለአንዳንድ ሴቶች ደግሞ ምንም የደም መፍሰስ አያጋጥማቸውም። አሁንም በዚህ ሳምንት ጤናማ እርግዝና እንዲኖራችሁ አንዳንድ የአኗኗር ለውጦችን ማድረግ ይኖርባችኋል። ማለትም የቅድመ ወሊድ ቫይታሚን መውሰድ, መጠነኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እና አልኮልን ማስወገድ እና ካይፌን አወሳሰዳችሁን መቀነስ ይኖርባችኋል። የ 3 ሳምንታት ነፍሰ ጡር ስትሆኑ በእውነቱ እርጉዝ መሆናችሁን ላታውቁ ትችላላችሁ። ፅንሰት የተካሄደው ከጥቂት ቀናት በፊት ነው። ነገር ግን በዚህ ሳምንት ውስጥ የወር አበባችሁ አይቀርም። 📌ህፃኑ በ 3 ኛው ሳምንት ምን ይመስላል? በ3 ተኛው ሳምንት ህፃኑ ገና ህዋስ ነው። ማለትም በማህፀን ቱቦ ውስጥ ወደ ተመሳሳይ ህዋስ እየተከፋፈለ የሚሄድ ህዋስ ነው። 📌የ 3 ሳምንት አልትራሳውንድ ምን ይመስላል ? morula ተብሎ የሚጠራው የዳበረው እንቁላል ከጨው ቅንጣት ያነሰ ነው። እናም በእንቅስቃሴ ላይ ነው። ነገር ግን ልክ 4 ሳምንት ስትገቡ  ዶክተራችሁ የማኅፀናችሁ ሽፋን እየወፈረ ሲሄድ ማየት ይችላል። ይህም ትንሹ ሞሩላ እንዳለበት የሚያሳይ ምልክት ነው። 📌 በ 3 ኛው ሳምንት የእርግዝና ምልክቶች ምን ይመስላሉ ? የ 3 ሳምንታት ነፍሰ ጡር ስትሆኑ ምልክቶቹ ገና ላይታዩ ይችላሉ። ይህ የሆነበት ምክንያት አብዛኛው የእርግዝና የመጀመሪያ ምልክቶች የሚከሰቱት በእርግዝና ሆርሞኖች ነው። እና ምናልባት እስካሁን በሰውነታችሁ ውስጥ ሆርሞኖቹ በከፍተኛ ደረጃ ላይኖራችሁ ይችላል። 📌 በ 3 ሳምንታት እና በሚከተሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ የሚከሰቱ አንዳንድ የእርግዝና ምልክቶች- ➣የመትከል ደም መፍሰስ የዳበረው ​​እንቁላል ወደ ማህጸናችሁ ክፍል ውስጥ ሲገባ ይህን ምልክት ልታዩ ትችላላችሁ። ➣ማቅለሽለሽ የጠዋት ህመም በመባል የሚታወቅ ሲሆን የእርግዝና ሆርሞን hCG በአዲሱ ነፍሰ ጡር አካላችሁ ውስጥ ማለፍ ሲጀምር፣ የሚከሰት ህመም ነው።በጣም ከባድ የማቅለሽለሽ ነገር ከገጠማችሁ የመንታ እርግዝና ምልክት ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም መንታ የምትፀንስ ሴት ከፍተኛ የሆነ የእርግዝና ሆርሞን ስለሚኖራት ነው። ➣በጡታችሁ ላይ የሚታዩ ለውጦች ሰውነታችሁ ወተት ለማምረት መዘጋጀት ሲጀምር ጡቶቻችሁ መታመም ሊጀምሩ ይችላሉ ። ➣ የወር አበባ መቅረት ከ 28 ቀናት ያነሰ የወር አበባ ዑደት ካላችሁ ይህ ምልክት በ3ተኛው ሳምንት መጨረሻ ላይ ይከሰታል። 📌 አዎንታዊ የእርግዝና ምርመራ ውጤት መች ይገኛል ? የእርግዝና ምርመራ የወር አበባችሁ ከመቅረቱ በፊት ካደረጋችሁ ውጤቱ አሉታዊ ነው። ለምን HCG ገና አልተመረተም። ነገር ግን በ48 ሰዓት ውስጥ በእጥፍ ይጨምራል። ስለዚህም ከጥቂት ቀናት ወይም ከሳምንት በኋላ ሌላ ድጋሜ የእርግዝና ምርመራ አድርጉ። ነገር ግን በህክምና የምታደርጉት የደም ምርመራ ከሽንት ምርመራ በተሻለ ሁኔታ የHCG ሆርሞን መጠንን መለየት ይችላል። ስለዚህ በቤት ውስጥ ከሚደረግ ምርመራ ይልቅ በደም ምርመራ ነፍሰ ጡር መሆናችሁን የበለጠ ማወቅ ትችላላችሁ። 📌በ 3 ሳምንታት እርግዝና ላይ ምልክቶች በምን ያህል ፍጥነት መታየት ይጀምራሉ ? አንዳንድ ሴቶች በዚህ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ምንም ልዩነት አይሰማቸውም። ሌሎች ደግሞ የ 3 ሳምንታት የእርግዝና ምልክቶችን ማየት ሊጀምሩ ይችላሉ። የማቅለሽለሽ ስሜት ከተሰማችሁ እና ጡቶቻችሁ ከታመሙ፣ ያ የተለመደ ነው። በዚህ ሳምንት ውስጥ ሆዳችሁ ትንሽ ወጣ ሊል ይችላል። አብዛኛዎቹ ነፍሰ ጡር ሴቶች እስከ 12 ሳምንት ድረስ ሆዳቸው ከፍ አይልም። ስለዚህም በዚህ ሳምንት በየቀኑ የቅድመ ወሊድ ቫይታሚን ቢያንስ ቢያንስ 400 ማይክሮ ግራም ፎሊክ አሲድ መውሰድ ይኖርባችኋል። እስከ ሁለተኛ አጋማሽ ድረስ ዕለታዊ የካሎሪ መጠናችሁን መጨመር የለባችሁም። #youtube #እርግዝና #ጤና