እንኮይ!
Yitbarek Mengistu / Great Work Life Coaching
0:00 / 0:00
እንኮይ!
178 просмотров · 12 дней назад
Yitbarek Mengistu / Great Work Life Coaching
275 подписчиков
178 просмотров · 12 дней назад
አንዴ ብልጭ ብለህ
ህይወቴን አብርተህ
እኔን በአንተ ገልጠህ
እኔን አሳይተህ
ደስታን ለእኔ ሰጥተህ
እኔን ለእኔው ትተህ
ድምጽህን አጥፍተህ
አንተ በጊዜ ተመለስህ
ጌጤ ወዳጄ ሆይ
ውዴ የእኔ እንኮይ
ዛሬ የት ላግኝህ?
እንዲህ ስፈልግህ
ዛሬ የት ላግኝህ?
እንዲህ ስናፍቅህ
በደጄ ተጫውተህ
አይኔን አንከራተህ
በልቤ ላይ ውለህ
ቶሎ መመለስህ
ልቤኑ መስበርህ
ምን ነበር አደራህ?
ምን ነበር መልእክትህ?
ጌጤ ወዳጄ ሆይ
ውዴ የእኔ እንኮይ
ዛሬ የት ላግኝህ?
እንዲህ ስፈልግህ
ዛሬ የት ላግኝህ?
እንዲህ ስናፍቅህ
ባዝንም ተስፋ አልቆርጥም!
ሙሉው ቀን ሲመጣ
መገናኘት አይቀርም!
ተዋህደን የለ! ሁሌም በአንድ ላይ ነን
አይናችንን ከድነን
ልባችንን ከፍተን
በዘላለሙ ዓለም እንገናኛለን!
ጌጤ ወዳጄ ሆይ
ውዴ የእኔ እንኮይ
ዛሬ የት ላግኝህ?
እንዲህ ስፈልግህ
ዛሬ የት ላግኝህ?
እንዲህ ስናፍቅህ
ባዝንም ተስፋ አልቆርጥም
ሙሉው ቀን ሲመጣ
መገናኘት አይቀርም
ተዋህደን የለ ሁሌም በአንድ ላይ ነን
አይናችንን ከድነን
ልባችንን ከፍተን
በዘላለሙ ዓለም እንገናኛለን!
አዎ! አብረን እንኖራለን!
Yitbarek Mengistu
Associate Certified Life Coach