🔴Azilawe Weredechi በሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
ከርቤ ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙራት፣ምክረ አበው፣ሃይማኖታዊ ትረካና ጥቅሶች..
0:00 / 0:00
🔴Azilawe Weredechi በሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
199 просмотров · 2 нед. назад
ከርቤ ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙራት፣ምክረ አበው፣ሃይማኖታዊ ትረካና ጥቅሶች..
75 подписчиков
199 просмотров · 2 нед. назад
🛑ይህንን ቻናል Subscribe በማድረግ አገልግሎቱን ይደግፉ።ለወዳጅዎም በማጋራት የእግዚአብሔር ቃል እንዲዳረስ የበኩልዎን ይወጡ።
እግዚአብሔር ያክብርልን!!
🛑 ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፭ ቀን ያለው ወቅት ‹ዘመነ ጽጌ፤ ወርኀ ጽጌ›
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ አምልኮ መሠረት ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፭ ቀን ያለው ወቅት ‹ዘመነ ጽጌ፤ ወርኀ ጽጌ› ተብሎ ይጠራል፡፡ በግእዝ ቋንቋ ‹ጸገየ› ማለት ‹አበበ፤ አፈራ፤ በውበት ተንቆጠቆጠ፤ በደም ግባት አጌጠ፤ የፍሬ ምልክት አሣየ› እንደ ማለት ነው፡፡ ከዚሁ ግስ ላይ ‹ጽጌያት› ብሎ ስም ማውጣት ሲቻል አበባማ፣ ውበታማ፣ አበባ የያዘና የተሸከመ ለማለት ደግሞ ‹ጽጉይ› ይላል፡፡ በተለይም ዘመነ ጽጌ (ወርኀ ጽጌ) የምትከበረው በሀገራችን ከወቅቶች ሁሉ በጣም በሚወደደው የመፀው ወቅት ነው፡፡ በዚህ ምድር በልምላሜና በውበት በምትንቆጠቆጥበት ወቅት በየሳምንቱ እሑድ ከመንፈቀ ሌሊት ጀምሮ ማኅሌተ ጽጌ የሚቆሙትና ሰዓታት የሚያደርሱት ካህናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በአበባ፣ በትርንጎ፣ በሮማን፣ በእንጆሪ … እየመሰሉ ለፈጣሪ መዝሙርና ምስጋና ያቀርባሉ፡፡