Перейти к содержимому

ስንክሳር ሰኔ ፲፮/16 በዓለ አባ አቡናፍር ገዳማዊ ጻድቁ ተወልዶ ያደገው በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብፅ ነው። "በዚሕ ካሉት መነኮሳትና በበርሃ ካሉት..

ብስራት ነጋሪ ሚዲያ Bisrat Negari Media

0:00 / 0:00

ስንክሳር ሰኔ ፲፮/16 በዓለ አባ አቡናፍር ገዳማዊ ጻድቁ ተወልዶ ያደገው በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብፅ ነው። "በዚሕ ካሉት መነኮሳትና በበርሃ ካሉት..

17 просмотров · 3 мес. назад
ብስራት ነጋሪ ሚዲያ Bisrat Negari Media
4,25 тыс. подписчиков
17 просмотров · 3 мес. назад
ስንክሳር ሰኔ ፲፮ |16 ✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞ ❖ እንኳን አደረሳችሁ ❖ ❖ ሰኔ 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት +"+ ቅዱስ_አቡናፍር ገዳማዊ +"+ =ጻድቁ ተወልዶ ያደገው በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብፅ ነው:: ወቅቱ ሥርዓተ መነኮሳት የሚጠበቅበት:አበው ባሕታውያን እንደ ሰማይ ከዋክብት በዝተው የደመቁበት ነበር:: ታላቁ አቡናፍርም ከክርስቲያን ወላጆቹ ተወልዶ: በሥርዓት አድጎ: መጻሕፍትንም ተምሮ ገና በወጣትነቱ መንኗል:: +ሥርዓተ መነኮሳትን ከአባ ኤስድሮስ ታላቁ አጥንቶ ገዳሙንና መምሕሩን እየረዳ ለብዙ ዓመታት በጾምና በጸሎት ኑሯል:: መነኮሳቱ ስለ ትሕትናውና ስለ ታዛዥነቱ ፈጽመው ያከብሩት ነበር:: +ከዕለታት በአንዱ ቀን አረጋውያን መነኮሳት ጭው ባለ በርሃ ስለሚኖሩ ባሕታውያን ሲጨዋወቱ: ሲያደንቁዋቸውም ሰማ:: እርሱ በዛ ወቅት ባሕታውያን በበርሃ መኖራቸውን አያውቅም ነበርና ሒዶ መምሕሩን አባ_ኤስድሮስን ጠየቃቸው:: እርሳቸውም "አዎ ልጄ! ከዚሕ በጣም ርቅው: ንጽሕናቸውን ጠብቀው: ከሰውና ከኃጢአት ተይለው የሚኖሩ ገዳማውያን አሉ" አሉት:: +ቅዱስ አቡናፍር "በዚሕ ካሉት መነኮሳትና በበርሃ ካሉት ማን ይበልጣል?" ቢላቸው "እነርሱ በጣም ይበልጣሉ:: ዓለም እንኩዋ ከነ ክብሯ የእግራቸውን ሰኮና አታህልም" አሉት:: ይሕንን የሰማው ቅዱስ አባ አቡናፍር ጊዜ አላጠፋም:: +ከመምሕሩ ቡራኬ ተቀብሎ ወደ በርሃ ሔደ:: ለብዙ ቀናት ከተጉዋዘ በኋላ አንድ ባሕታዊ አግኝቶ አብሯቸው ተቀመጠ:: ከእርሳቸው ዘንድም ሥርዓተ ባሕታውያንን ተምሮ እንደገና ወደ ዋናው በርሃ ጉዞውን ቀጠለ:: +ከብዙ ቀናት መንገድ በኋላም አንድ ሠፊ ሜዳ ላይ ደረሰ:: አካባቢው የውሃ ጠብታ የማይገኝበት: ይቅርና መጠለያ ዛፍ የሣር ዘር እንኩዋ የሌለበት ወይም በልሳነ አበው "ዋዕየ ፀሐይ የጸናበት: ልምላሜ ሣዕር የሌለበት: ነቅዐ ማይ የማይገኝበት" ቦታ ነበር:: በዚህ ቦታ ይቅርና የሰው ልጅ አራዊትም አይኖሩበትም:: +ለአባ አቡናፍር ግን ተመራጭ ቦታ ነበር:: ቅዱሳኑን ይሕ አያሳስባቸውም:: ምክንያቱም ለእነርሱ ምግባቸውም: ልብሳቸውም ፍቅረ_ክርስቶስ ነውና:: አባ አቡናፍር ወደ ፈጣሪ ጸለዩ:: በእግዚአብሔር ቸርነት ከጎናቸው አንዲት ዘንባባ (በቀልት) በቀለች:: ከእግራቸው ሥርም ጽሩይ ማይ (ንጹሕ ምንጭ) ፈለቀች:: +ጻድቁ ተጋድሏቸውን ቀጠሉ:: ዓመታት አለፉ:: ልብሳቸውን ፀሐይና ብርድ ጨርሶት ቅጠል ለበሱ:: በዚያ ቦታም የሰው ዘርን ሳያዩ ለ60 ዓመታት በተጋድሎ ኖሩ:: የሚያርፉበት ጊዜ ሲደርስ እግዚአብሔር አባ_በፍኑትዮስን (የባሕታውያንን ዜና የጻፈ አባት ነው) ላከላቸው:: +ቃለ እግዚአብሔርን እየተጨዋወቱ ሳለ የአባ አቡናፍር አካሉ ተለወጠ:: እንደ እሳትም ነደደ:: አባ በፍኑትዮስም ደነገጠ:: ታላቁ ገዳማዊ ግን እጆቻቸውን ዘርግተው ጸለዩ: ሰገዱና አማተቡ:: ነፍሳቸውም ከሥጋቸው በፍቅር ተለየች:: ቅዱሳን መላዕክትም በዝማሬና በማኅሌት አሳረጉዋት:: የሚገርመው ደግሞ አባ በፍኑትዮስ ይሕን ሲያይ ቆይቶ ዘወር ቢል ዛፏ ወድቃለች: ቅርንጯም ደርቃለች:: =ዳግመኛ ይህች ዕለት የቅዱሳን አበው ባሕታውያን መታሠቢያ ናት:: +ከሰው (ከዓለም) ርቀው: ንጽሕ ጠብቀው: ዕጸበ ገዳሙን: ግርማ አራዊቱን: ጸብዐ አጋንንትን ታግሠው የኖሩ: ስማቸውን የምናውቀውንም ሆነ የማናውቃቸውን እንድናከብራቸው ቤተ_ክርስቲያን ሥርዓትና በዓል ሠርታለች:: =አምላካችን ከአበው ባሕታውያን ጸጋ በረከት ይክፈለን:: =ሰኔ 16 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.አባ አቡናፍር ገዳማዊ (ስም አጠራሩ የከበረ: ሽምግልናው ያማረ አባት) 2.አበው ቅዱሳን ባሕታውያን ( ዛሬ የሁሉም ቅዱሳን_ባሕታውያን (በተለይም የስውራኑ) ዓመታዊ በዓል ነው:: ¤ከሰው: ከዓለምና ከኃጢአት ርቀው ¤ንጽሕ ጠብቀው ¤ዕጸበ ገዳሙን ¤ድምጸ አራዊቱን ¤ግርማ ሌሊቱን ¤የሌሊቱን ቁር ¤የመዓልቱን ሐሩር ¤ረሐቡን: ጽሙን: መራቆቱን . . . ሁሉ ስለ ፍቅረ_ክርስቶስ ሲሉ ታግሠውታልና:: ዛሬም በየበርሃው የወደቁ: ስለ ዓለም ምሕረትን የሚማጸኑ አሉ:: አምላካቸው በረከታቸውን ያድለን 3.የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ከግብጽ እንዲመለስ የነገረበት (ተዝካረ ሚጠታ ለእግዝእትነ ማርያም) 4.አፄ ይኩኖ አምላክ (ንጉሠ ኢትዮዽያ) ❖ወርኃዊ በዓላት 1፡ ኪዳነ ምሕረት ማርያም 2፡ ቅድስት ኤልሳቤጥ 3፡ አባ ዳንኤል ገዳማዊ 4፡ ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሠ ሮሜ 5፡ አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ 6፡ ቅዱስ ሐርቤ ንጉሠ ኢትዮጵያ +"+ . . . ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ: ከዚሕም በላይ በእሥራትና በወኅኒ ተፈተኑ . . . ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ: እየተጨነቁ: የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ:: ዓለም አልተገባቸውምና በምድረ በዳና በተራራ: በዋሻና በምድር ጉድጉዋድ ተቅበዘበዙ:: +"+ (ዕብ. 11:36) ወስብሐት ለእግዚአብሔር ╭══•|❀:✞✟✞❀|•══╮ ✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥ ➡ ለወዳጅ ዘመድ ያጋሩት(Shere) በመንፈሳዊ ትህትና እጠይቃለሁ❤ 𝑭𝒐𝒍𝒍𝒐𝒘𝒆𝒓𝒔.👇 @Bisrat Negari Media 🔎ፌስቡክ ገፅ ፦ Facebook https://www.facebook.com/profile.php?... @Bisrat Negari Media 🔎#ዩቲዩብ ገፅ፦ YouTube    / @bisratnegarikidusgebrel   @Bisrat Negari Media 🔎 ቲክቶክ፦ Tiktok tiktok.com/@bisratnegarimedia @Bisrat Negari Media 🔎ቴሌግራም ገፅ፦ Telegram https://t.me/bisratnegarikidusgebrel ✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥ ╰══•|❀:✞✟✞❀|•══╯ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር