ጊዜ ስጠኝ! ኢዮብ አሊ ( Eyob Ali) New Amharic protestant gosple song!!
Eyob Ali Official
0:00 / 0:00
ጊዜ ስጠኝ! ኢዮብ አሊ ( Eyob Ali) New Amharic protestant gosple song!!
283 058 просмотров · 5 л. назад
Eyob Ali Official
16,7 тыс. подписчиков
283 058 просмотров · 5 л. назад
አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው።
ያዕቆብ 1:26
Note: Unautorized distribution and re- upload of this
content is strictly prohibited.
This is my official youtube channel. Please subscribe!
Facebook: / eyobali2
Telegram: https://t.me/Eyob_Ali2
©Eyob Ali
ካንድ አፍ ላይ እልፍ ልሳኖች ሳያርፉ ከሚያወሩበት
ሁካታ ዘውዱን ደፍቶ ዝምታ ካንቀላፋበት
ከግፊያው ከግርግሩ ከለቅሶው ከደስታው ቅኝት
አግልለኝ ብቻዬን ልሁን ጊዜ ስጠኝ ራሴን ልስማበት
መዝሙር አለ መድረኩ ላይ ቅኔ ይፈልቃል
ቃል ሲገለጥ እንኳን ህያው ሙቱ ይሰማል
ጥናው በዝቶ ጉባኤውን ጢስ ሞልቶታል
በነጭ አልባስ ሁሉም ደምቆ ሰማይ መስሏል
ግን ያልነፃ መስዋእት ህይወት አልባ ቁርባን
የቀለለ አምልኮ የማይደፋ ሚዛን
በድምፅ/ድምፄን/ አዋዝቼ ወደ ሰማይ ልኬ ተቀባይ ስላጣ
ጩኸት ብቻ ሆኖ የገደል/ እየገጫጨ/ ማሚቶ ተመልሶ መጣ
በንፁህ ልብ በተሰራ አእምሮ
በፅድቅ ሀሳብ ኑሮ ተጨምሮ
በተገዛ መንፈስ በትህትና ጥልቀት
ወደምቀርብበት አንተ ወዳለህበት
ፈቀቅ አርገኝ ህይወት ላዚምበት/ ላሽትትበት
በሌለህበት ጫጫታ
ባልከበርክበት እልልታ
ባላለፍክበት ግርታ
አሞኛል ተሰልፌ ካልቆምኩበት ቦታ
አሞኛል ከደረቅ እርሻ ፍሬ ስጠብቅ
"" ከጠራው ሰማይ ዝናብ ስናፍቅ
""" ባዶ ዙፋን ፊት ስል ቁጭ ብድግ
"" ባላለፍክበት ዱካ ስፈልግ
ጊዜ ስጠኝ ×፫
ጊዜ ስጠኝ ጌታ
መስታወቴን ይዜ ልሂደሰ ወደ ፀጥታ
ይቀመጥ ልቤ አንተ ቦታ
ራሴን ላድምጥ በፀጥታ
የት ጋር እንዳለው በመንገዴ
ልቁም ላስተውል እስኪ ላንዴ
ይቀመጥ ልቤ አንተ ቦታ
ጥሞናን ልውሰድ በፀጥታ
የት ጋር እንዳለው በህይወት ገፄ
ልቁም ላስተውል ጠፍቶ ድምፄ