የዘመናዊቷ ኢራን ወታደራዊ ‘አርክቴክት! ’የጀነራል ሱሌይማኒ ውርስ በተመድ ጉባዔ? | GEN Soleimani's Legacy at the UN?
GEBEYA GLOBAL
0:00 / 0:00
የዘመናዊቷ ኢራን ወታደራዊ ‘አርክቴክት! ’የጀነራል ሱሌይማኒ ውርስ በተመድ ጉባዔ? | GEN Soleimani's Legacy at the UN?
889 просмотров · 1 час назад
GEBEYA GLOBAL
128 тыс. подписчиков
889 просмотров · 1 час назад
ቤንጃሚን ኔታንያሁ በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር ለማድረግ ወደ መድረክ ሲወጡ የበርካታ ሃገራት ልኡካን አደራሹን ለቀው በመውጣት ተቃውሟቸውን ሲገልፁ ተመልክተናል። የኢራን ልኡካን ቡዱንም አደራሹን ለቀው በመውጣት ተቃውሟቸውን የገለፁ ሲሆን ነገር ግን የዝነኛው ጄነራል ቃሲም ሱሌይማኑ ምስል በጠረጴዛቸው ትተው የወጡበት አጋጣሚ በበርካቶች ዘንድ መነጋገርያ የሆነ ጉዳይ ሁኗል። ለመሆኑ ግን እኚህ በጊዜያቸው ከአያቶላህ አሊ ኻሜኔ ቀጥሎ በኢራን ውስጥ ተፅእኖ ፈጣሪ ነበሩ የሚባሉት የጦር አዛዥ ማን ነበሩ?
የኢራን አብዮታዊ ዘብ የቁድስ ኃይል መሪ የነበሩት ሜጀር ጄነራል ቃሲም ሱሌይማኒ እ.ኤ.አ. ጃንዋሪ 3 ቀን 2020 በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በባግዳድ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አቅራቢያ በተፈጸመ የሰው አልባ አውሮፕላን ድሮን ጥቃት ነበር የተገደሉት። ሱሌይማኒ ከአያቶላህ አሊ ኻመነይ ቀጥሎ በኢራን ሁለተኛው በጣም ኃያል እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰው እንደሆኑ ይቆጠሩ የነበሩ ሲሆን፡ በሀገሪቱ የውጭ ፖሊሲ ላይ ከኢራን ፕሬዝዳንት በላይ ከፍተኛ ስልጣን እና ተፅዕኖም ነበራቸው።
ከ1998 ጀምሮ የቁድስ ኃይል አዛዥ ሆነው ሲያገለግሉ፡ በመካከለኛው ምስራቅ የኢራንን የፕሮክሲ ኃይሎች እና ሚሊሻዎች በሊባኖስ ሄዝቦላህ፣ በኢራቅ የሚገኙ የሺአ ሚሊሻዎች እና በሶሪያ ያሉ ታጣቂዎችን በበላይነት በመምራት የኢራን ቀጣናዊ ወታደራዊ ስትራቴጂ ዋነኛ አርክቴክት ነበሩ። ታድያ እኛም ዛሬ እኝህ መሪ እንቃኛቸው አለን። ኣብራችሁን ቆዩ!
As we witnessed, when Benjamin Netanyahu took the stage to address the UN General Assembly, delegations from numerous countries walked out of the hall to express their protest. The Iranian delegation also walked out in protest, but a notable moment that became a talking point for many was that they left a picture of the famous General Qasem Soleimani on their desk. By the way, who was this military commander who, in his time, was considered the most influential person in Iran right after Ayatollah Ali Khamenei?
Major General Qasem Soleimani, the leader of the Islamic Revolutionary Guard Corps (IRGC) Quds Force, was killed on January 3, 2020, in a drone strike near the Baghdad International Airport ordered by President Donald Trump. Soleimani was considered the second most powerful and influential person in Iran after Ayatollah Ali Khamenei, holding higher authority and influence over the country's foreign policy than the Iranian president.
Serving as the commander of the Quds Force since 1998, he was the chief architect of Iran's regional military strategy by overseeing Iran's proxy forces and militias in the Middle East, including Hezbollah in Lebanon, Shia militias in Iraq, and militants in Syria. Therefore, today we are taking a look at this leader. Stay with us!
#GebeyaGlobal #GlobalSpecialProgram #GlobalPodcast #GlobalNews #GlobalAnalysis #BenjaminNetanyahu #UNGA #QasemSoleimani #Iran #US #MiddleEast #Geopolitics #IRGC