2. ያዕቆብ፦ መግቢያ
Evangelist Yared Tilahun
0:00 / 0:00
2. ያዕቆብ፦ መግቢያ
33 603 просмотра · Трансляция закончилась 4 года назад
Evangelist Yared Tilahun
69,1 тыс. подписчиков
33 603 просмотра · Трансляция закончилась 4 года назад
መግቢያ እንደ ስሙ መግቢያ በር ነው። ወደ አንድ ትልቅ ቤት ውስጠኛ ክፍል ለመዝለቅና በውስጡ ያሉትን በረከቶች ለመካፈል በበሩ ማለፍ ግድ ይላል። በመስኮት የሚገባ ሌባ እንጂ ባለቤት ሊሆን አይችልምና በበሩ ለመግባት እንገደዳለን። በዚህ በያዕቆብ መልዕክትም ውስጥ በእያንዳንዱ ቁጥር፣ አንቀጽና ምዕራፍ ውስጥ የተሰወሩትን ዕንቁዎች ለመቃረም ማን ጻፈው፣ ለነማን ጻፈው፣ ለምን ጻፈው፣ መቼ ጻፈው … ወ.ዘ.ተ የሚሉትን የመግቢያ ጥያቄዎች መመለስ ይኖርብናል። እነዚህን ጥያቄዎች መመለስ ከንቱ ልፋት የሚመስላቸው ወገኖች ጥቂት አይደሉም። ሆኖም ለቀጣይ ጥናታችን ወሳኝ ነውና በመጠኑም ቢሆን እንሄድበታለን። ጥሩ አገባብ፣ ለጥሩ አቆያይ መሠረት ነውና መልካም ቆይታ እመኝላችኋለሁ።