የእመቤታችን ስደት |በዘመነ ፅጌ |በወርኃ ፅጌ |ጽጌ ማርያም || Tsigemariam | Zemen Tsige | እንኳን አደረሳችሁ!
Betemariam
0:00 / 0:00
የእመቤታችን ስደት |በዘመነ ፅጌ |በወርኃ ፅጌ |ጽጌ ማርያም || Tsigemariam | Zemen Tsige | እንኳን አደረሳችሁ!
389 просмотров · 3 нед. назад
Betemariam
8,58 тыс. подписчиков
389 просмотров · 3 нед. назад
#ዘመነ_ፅጌ #ወርኃ_ፅጌ #ጽጌማርያም
#የእመቤታችን_ስደት
ከመስከረም ፳፮ እስከ ኅዳር ፮ ቀን ድረስ ያሉትን ፵ ቀናት የሚያጠቃልለው ክፍለ መጸው ዘመነ ጽጌ /ወርኀ ጽጌ› ተብሎ ይጠራል ፡፡
‹ዘመነ ጽጌ› ‹የአበባ ወቅት፣ የአበባ ጊዜ፣ የአበባ ዘመን› እንደ ማለት ነው፡፡ ይህ ወቅት ዕፀዋት በአበባ የሚያጌጡበት፣ ምድር በአበቦች ኅብረ ቀለማት የምታሸበርቅበት፣ ወንዞች ንጹሕ የሚኾኑበት፣ ጥሩ አየር የሚነፍስበት፣ አዕዋፍ በዝማሬ የሚደሰቱበት፣ የሰው ልጆች ‹‹አሠርጎካ ለምድር በሥነ ጽጌያት፤ አቤቱ ምድርን በአበቦች ውበት አስጌጥሃት›› እያሉ የዘመናት አስገኚና ባለቤት የኾነውን ልዑል እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑበት፤ ከዚህም ባሻገር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከተወደደ ልጇ ከጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ከገሊላ ወደ ግብጽ ምድር መሰደዷን የምናስብበት ወቅት ነው፡፡