Hamlet Beljun | WEDU EYESUSE | “ውዱ ኢየሱሴ ” - New Ethiopian Gospel Music Videos 2026/2018
Hamlet Beljun
0:00 / 0:00
Hamlet Beljun | WEDU EYESUSE | “ውዱ ኢየሱሴ ” - New Ethiopian Gospel Music Videos 2026/2018
12 994 просмотра · 7 ч назад
Hamlet Beljun
40,3 тыс. подписчиков
12 994 просмотра · 7 ч назад
ውዱ ኢየሱሴ
"በደም የፃፍከውን የፍቅር ደብዳቤ፤
ወጣሁ ከሞት ሀገር አምኜ አንብቤ።
ሞልቶ ከተረፈው የገባኝ ጥቂቱ፤
የተወደድኩበት እንደሆነ ብርቱ።"
"ፍቅር የሚጨበጥ፣ ፍቅር የሚዳሰስ፤
ሰሙ ህብረ-ቃሉ፣ ወርቁም—ኢየሱስ!"
ባንተ ቁስል ባንተ የመስቀል ሞት፣
ተችሮኛል ህይወት።
ባንተ ቁስል ባንተ የመስቀል ሞት፣
ገባሁ ህያዋን ህብረት።
"ባንተ ይቅርታ፣ ባንተ ምህረት፤
ተችሮኛል ህይወት።
ባንተ ይቅርታ፣ ባንተ ምህረት፤
ገባሁ ህያዋን ህብረት።
"ደርሶ ሊተካከል ሚዛን ላይ ባይውልም፤
ያየኝን አይቼ ወድጃለሁ እኔም።
ታትሟል በነፍሴ የነፍስህ ውለታ፤
ምንም አይመዝንም በፍቅርህስ ፈንታ።
"የኔ ህይወት፣ እስትንፋሴ፤
ኢየሱሴ—ውዱ ኢየሱሴ!"
"እንኳንስ በድዬህ ውድዬ፣ ኖሬልህ አይበቃም፤
ይቺን ጥቂት እድሜ፣ የአንተን ከአለም አላብቃቃም።
አቅም ስጠኝና አሁንም አብዝቼ ልጠጋህ፤
አንተን እየወደድኩኝ ልሁን ጠበኛ ከአለም ጋር።
"ውዴ ኢየሱስ እንዳልኩህ ጠጋ፤
ይለቅልኝ እድሜዬ አንተጋ።
ውዴ ኢየሱስ ብዬ አንተን ጥብቅ፤
የህይወቴ ጀምበሯ ይጥለቅ!