ሐርድ ዉስጥ ነን | hard wust nen | በሽመልስ ስዩም ተፃፈ
የምልከታ ትረካዎች (milketa tv)
0:00 / 0:00
ሐርድ ዉስጥ ነን | hard wust nen | በሽመልስ ስዩም ተፃፈ
122 просмотра · 4 дня назад
የምልከታ ትረካዎች (milketa tv)
2,37 тыс. подписчиков
122 просмотра · 4 дня назад
ሽመልስ ስዩም በ1990ዎቹ አጋማሽ አካባቢ በአዲስ አበባ ዩኒርሲቲ የፍልስፍና ትምህርት ክፍልን ሲከታተል የነበረና በአብዛኛዉ በዩኒርሲቲዉ ባለዉ የባህል ማእከል ያቀርባቸዉ በነበሩ የስነ-ፅሁፍ ስራዎቹ በዩኒርሲቲዉ ማህበረሰቦችና ተማሪዎች ዘንድ ይታወቅ ነበረ:: ከዛም አስቀድሞ ባደገበት እና ወጣትነቱን ባሳለፈባት የሸዋዋ ደብረ ብርሃን ከተማ ዉስጥ ተመስርቶ በነበረዉ አፍሮ ብሶል የስነፅሁፍና የትያትር ማህበር ዉስጥ በስነ-ፅሁፍ፣ በትወናና በአመራርነትም ጭምር ሲያገለግል የቆየ ተወዳጅ ስነ ምግባር ያለዉና ጨዋታ አዋቂ ሰዉ ነበረ:: ሽመልስ ጋር በአማተርነት አብሬዉ በመስራት የማዉቀዉ የነበረ ሲሆን ይህን ለርሱ አንድ የሆነዉን ሥራዉን ሳቀርብላችሁ ለርሱ መታሰቢያነት ይሆን ዘንድ በመመኘት ነዉ:: እነሆ ከምረቃ በኋላ በድንገተኛ ህመም ከዚህ አለም ቢለይም ስራዎቹና ትዝታዉ ግን በምናዉቀዉ በእኛ ዘንድ ሕያዉ ሆነዉ በክብር እስካሁን አሉ::
ነፍስህን በመልካሞቹ ተርታ ያቆይልን ወንድማለም::