Перейти к содержимому

ሰግዶ ሲመለስ || Segdo Simeles Track - 04 Segdo Simles EP Album 2018/2026

Exodus Sound

0:00 / 0:00

ሰግዶ ሲመለስ || Segdo Simeles Track - 04 Segdo Simles EP Album 2018/2026

3 832 просмотра · 2 недели назад
Exodus Sound
925 подписчиков
3 832 просмотра · 2 недели назад
ሰግዶ ሲመለስ እድሜውን ሙሉ ወንበዴ ሲሆን ቀርቦ ያላየው በሀጥያት ውሎ በሞት ሊቀጣ ብርሃን ሳያየው በቀኑ ማምሻ ሊቀጣ ሲቀርብ በዛ እንዳይጠፋ ቀጠሮ ይዟል ወዶታልና አብረው ተሰቅለው ለርሱ መሞቱን ቀድሞ አብስሮታል የጊዜ መለኪያ ከፍጥረት የኖረው ለዘገየው ቢረፍድ የማይደርስ ቢመስለው ለጌታ አልረፈደም ጊዜን እንኳን ያዛል ሚዘገይ ቢመስልም በርግጥ ደርሶለታል አቤት ምህረቱ የጌታ ውለታ ፈቅዶ ይታገሳል ሁሉ እስኪመጣ የሚምረውን እርሱ ይምረዋል ለሚራራለት ይራራለታል! ሰግዶ ሲመለስ የወደደውን አምላክ ፈልጎ ኢሳያስ ከፍቶ ባይረዳውም ሚለው መልዕክቱ ገልጦ እንዲያስረዳው በጌታ መንፈስ ፊልጶስ ታዟል ጃንደረባውም በሰፊ እጆቹ፣ በፍቅሩ ታቅፏል ፈልጌው ራቀኝ ወድጄውም ጠላኝ የሚለው ማን አለ ደፍሮ የሚናገር የጠላውን እንኳን ደማስቆ መንገድ ላይ ከሰማይ ተገልጦ ተመለስ ይለዋል አቤት ምህረቱ የጌታ ውለታ ፈቅዶ ይታገሳል ሁሉ እስኪመጣ የሚምረውን እርሱ ይምረዋል ለሚራራለት ይራራለታል!