Перейти к содержимому

#ቅኔን ያውጣ | Kinen Yawuta | ዘማሪ ዲያቆን ሄኖክ ማርቆስ | Zemari Dn Henok Markos

Deacon Henok Official и ещё 3

0:00 / 0:00

#ቅኔን ያውጣ | Kinen Yawuta | ዘማሪ ዲያቆን ሄኖክ ማርቆስ | Zemari Dn Henok Markos

387 просмотров · 8 дн. назад
Deacon Henok Official и ещё 3
387 просмотров · 8 дн. назад
ቅኔን ያውጣ ቅኔን ያውጣ አፌ ውለታሽን ላውራ ጨለማውን አለፍኩ ድንግል ካንቺ ጋራ ልክ እንደ በላኤሰብ ታደግሽኝ እናቴ በምልጃሽ ቆምያለሁ ታድሳ ህይወቴ የኃጢአት ጎተራ ማደሪያው ነበርኩኝ ልጅነቴን ሸጬ በዓለም የታወርኩኝ ውሎና አዳሬ በግፍ የታጠረ ህልሜና ምኞቴ የከንቱ ነበረ     ይህ ሁሉ በምልጃሽ ተጠቅሎ አልፎ     ይኸው እዘምራለሁ ልቦናዬ አርፎ ከአንደበቴ ክፋት ተንኮልም ከግብሬ እጅግ ከብዶኝ ነበር የበደል ቀንበሬ በጠላት ግዞት ስር ተገዝቼ ምታይ ከቃላቶች በላይ ነበር የእኔ ስቃይ      ያቀለልሽው ሸክሜ አያልቅም ተነግሮ      ስምሽ ስንቅ ሆኖኛል ቤቴን አሳምሮ የቀደመ ፍቅሬን እረስቼ የተውኩ ሲጠቋቆሙብኝ በሰው የተነቀፍኩ በስራዬ ሁሉ አምላኬን የተዉኩኝ ኃጢአተኛ ሲባል ምሳሌ ነበርኩኝ       ዛሬ ግን ታድሼ ወጥመዴ ተሰብሮ       አወደስኩሽ ድንግል ልመናዬ ሰምሮ በአለም መአዛ ብልጭልጭ ተስቤ7 ትዕቢት ፍቅረነዋይ ሞልቶብኝ በልቤ በቃኝ ብዬ የወጣሁ የአባቴን ቤት የተውኩ ያ የጠፋው ልጅሽ ድንግል እኔ ነበርኩ       በእናትነት ጥላሽ ሁሉን ተሻግሬ       እቀኝልሻለሁ በምስጋና ዛሬ ግጥም ዲያቆን አስቻለው ሸዋ ዜማ ዘማሪ ዲያቆን ዘላለም ታከለ ክራር አንተነህ ተክለማርያም መሰንቆ እንዳልካቸው አዱኛ ዋሽንት ሳይመን አረጋይ  Motion & Graphics ዲ ሔኖክ +251968240051    / @deaconhenokofficial