Перейти к содержимому

የ ፳፻፲፰ ዓ.ም /2026/ የመንፈሳዊ ትምህርት ዓመት ምርቃት ላይ በልጆች የቀረበ ልዩ መርዓግብር።

EOTC Cologne St.Michael ኮሎኝ ቅዱስ ሚካኤል AEOKD Germany

0:00 / 0:00

የ ፳፻፲፰ ዓ.ም /2026/ የመንፈሳዊ ትምህርት ዓመት ምርቃት ላይ በልጆች የቀረበ ልዩ መርዓግብር።

340 просмотров · 2 месяца назад
EOTC Cologne St.Michael ኮሎኝ ቅዱስ ሚካኤል AEOKD Germany
716 подписчиков
340 просмотров · 2 месяца назад
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ በጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት የርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ኮሎኝ/ቦን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን /በፈለገ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት/ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምርት ለተከታተሉ ሕፃናትና አዳጊ ልጆች የምስክር ወረቀት ሰጠች። ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም። ምሳሌ ፳፪ ፥ ፮ Wie man einen Knapen gewöhnt,so läßt er nicht davon,wenn er alt wird."Sprüche 22:6 ልጆቹ የምስክር ወረቀቱን ለማግኘት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፥ የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት፥ የርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ኮሎኝ/ቦን ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን /የፈለገ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት/ ሥር በ ፳፻፲፰ ( 2026 ) ዓ.ም. የትምህርት ዓመት የተሰጠውን "የሃይማኖት ትምህርት ( መሠረተ ሃይማኖት)፥ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፥ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፥ መዝሙር፥ እንዲኹም የአማርኛ ፊደል (ገበታ) ክፍል አንድ እና ሁለት" በአግባቡ መከታተላቸው ተገልጿል:: በመርኀግብሩም ሕፃናትና አዳጊ ልጆች እስከ ዛሬ የተማሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፤ የአማርኛ ፊደል በምሳሌ ማቅረብ፤ እንቆቅልሽ፤ እና ያሬዳዊ ዝማሬን በማቅረብ የደረሱበትን በአባቶችና የደብሩ ምእመናን ፊት አስመስክረዋል። በደብሩ ለልጆች የሚዘጋጀው ዘርፈ ብዙ የሆነው የማስተማሪያ መርኀ ግብር ቀጣይነት ያለው እንደሚሆን የተገለጠ ሲሆን ወደፊትም እስካሁን ያልጀመሩትን ሊያነቃቃ እንደሚችል ተስፋ ተጥሎበታል:: ሕፃናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተዉ አትከልክሏቸው፥ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ናትና። ማርቆስ ፲ ፥ ፲፬ ,,Lasset die Kinder zu mir kommen und wehret ihnen nicht.Denn solcher ist das Reich Gottes.''Markus 10:14 EOTC Cologne St.Michael በጀርመን የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ኮሎኝ/ቦን ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ሐምሌ ፲፪ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም. Juli 19/2026