🔴ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን? | ዳን. 3÷24 | ዲያቆን ዘላለም ታዬ | ፍኖተሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት| Finote hiwot
Finote Hiwot ፍኖተ ሕይወት
0:00 / 0:00
🔴ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን? | ዳን. 3÷24 | ዲያቆን ዘላለም ታዬ | ፍኖተሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት| Finote hiwot
436 просмотров · 9 мес. назад
Finote Hiwot ፍኖተ ሕይወት
4,65 тыс. подписчиков
436 просмотров · 9 мес. назад
ትንቢተ ዳንኤል 3÷24-28
የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ፤ አማካሪዎቹንም። ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን? ብሎ ተናገራቸው። እነርሱም። ንጉሥ ሆይ፥ እውነት ነው ብለው ለንጉሡ መለሱለት።
እርሱም እነሆ፥ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም፤ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል ብሎ መለሰ።
የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር ወደሚነድደው ወደ እሳቱ እቶን በር ቀርቦ። እናንተ የልዑል አምላክ ባሪያዎች፥ ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም፥ ኑ ውጡ ብሎ ተናገራቸው። ሲድራቅና ሚሳቅም አብደናጎም ከእሳቱ መካከል ወጡ።
መሳፍንቱና ሹማምቶቹም አዛዦቹና የንጉሡ አማካሪዎች ተሰብስበው እሳቱ በእነዚያ ሰዎች አካል ላይ ኃይል እንዳልነበረው፥ የራሳቸውም ጠጕር እንዳልተቃጠለች፥ ሰናፊላቸውም እንዳልተለወጠ፥ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው አዩ።
ናቡከደነፆርም መልሶ መልአኩን የላከ፥ ከአምላካቸውም በቀር ማንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፥ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ።
የቀጨኔ ደብረሰላም መድኀኔዓለም እና ደብረትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን ፍኖተሕይወት ሰንበት ትምህርት