🔴 "የአርምሞ እናት" ዲ ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ) || New EP Yiheg Fetsame | Ye armemo Enat l D Zelalem Takele
Deacon Zelalem Takele Official - ዲ ዘለዓለም ታከለ ዘጎላ
0:00 / 0:00
🔴 "የአርምሞ እናት" ዲ ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ) || New EP Yiheg Fetsame | Ye armemo Enat l D Zelalem Takele
75 858 просмотров · 2 г. назад
Deacon Zelalem Takele Official - ዲ ዘለዓለም ታከለ ዘጎላ
24,6 тыс. подписчиков
75 858 просмотров · 2 г. назад
#like #share #subscribe
የአርምሞ እናት
የአንደበት ፣ የብዕሯን ኃይል በጸጋዋ ብንመዝነው፥
የእሷን ስብከት ፣ የእሷን ጦማር የሚችል ስፍራ የቱ ነው?፥
የአምላክ እናት ፣ የአርምሞ እናት ዝምታዋ ግን ድንቅ ነው።
ከ22ቱ ፍጥረት 7ቱን በአርምሞ፥
የፈጠረ ልጇ በቀራንዮ ደግሞ፥
በሸላቾቹ ፊት ዝም እንደሚል ጠቦት፥
በአርምሞ አዳነን በሞቱ ገድሎ ሞት።
ግብሯም እንደ ልጇ ፣ መልኳም እንደ አምላኳ፥
ሁሉንም በልቧ መጠበቅ ታሪኳ፥
በሚልቅ ዝምታ ከአርሳኒ ፣ ከአጋቶን፥
ቃልን ከለከለች የቃል እናት ስትሆን።
የነቢያቱን ነው ጸሎትም ብታደርስ፥
አሰምታም ብትጮኽ ማርያም በመቅደስ፥
“ከነገረኝ በቀር ገብርኤል በብሥራት፥
ምንም አላውቅ” ‘ምትል እመ እኅትና ናት።
ባትጽፍ ፥ ከእርሷው እቅፍ ፣ አንድ ልጇ ወንጌል፥
ባ’ርምሞ ብትጸና እርሷ ግን ናት ፊደል፥
ቃል የተጻፈባት ጽሌ ናት ፣ ሰሌዳ፥
ሕይወቷን አንብበን ልጇን እንረዳ።
ግጥም ዲ ከሣቴ ብርሃን ገ/ኢየሱስ (ዶ/ር)
ዜማ ዲ ዘለዓለም ታከለ (ዘጎላ)
ክራር ዘ. ዘውዱ ጌታቸው
መሰንቆ እንዳልካቸው አዱኛ
ዋሽንት ኤልያስ ፈቃዱ
ድምጽ ቅጂ ሚክሲንግና ማስተሪንግ
ዘጎላ ሬከርድስ