Перейти к содержимому

🔴አዲስ( Aregach Besibhate) " ዐረገች በስብሐት " በዘማሪ ዲያቆን አማን ኡርጌሳ

ከርቤ ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙራት፣ምክረ አበው፣ሃይማኖታዊ ትረካና ጥቅሶች..

0:00 / 0:00

🔴አዲስ( Aregach Besibhate) " ዐረገች በስብሐት " በዘማሪ ዲያቆን አማን ኡርጌሳ

424 просмотра · 1 месяц назад
ከርቤ ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙራት፣ምክረ አበው፣ሃይማኖታዊ ትረካና ጥቅሶች..
55 подписчиков
424 просмотра · 1 месяц назад
🛑ይህንን ቻናል Subscribe በማድረግ አገልግሎቱን ይደግፉ።ለወዳጅዎም በማጋራት የእግዚአብሔር ቃል እንዲዳረስ የበኩልዎን ይወጡ። እግዚአብሔር ያክብርልን!! የእመቤታችን በዓለ ዕርገት በዚያን ጊዜ ወንጌላዊ ዮሐንስ እስያ በሚባል አገር እያስተማረ በነበረበት በነሐሴ ወር ዐሥራ ስድስተኛ ቀን ተድላ ደስታ ወደአለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቀ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስንም የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ካለበት ከዕፀ ሕይወት ዘንድ ተቀምጦ አየው፡፡ የንጽሕት እናቱንም ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው፤ እነርሱም ‹‹የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል›› አሏት፡፡ ያን ጊዜም ከዕፀ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ወጣ፡፡ ጌታችንም እንዲህ እያለ አረጋጋት፤ ‹‹የተወደድሽ የወለድሽኝ እናቴ ሆይ! ዘላለማዊ ወደ ሆነ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ ነዪ፡፡›› ከዚያም በገነት ያሉ ዕፅዋት ሁሉም አዘነበሉ፤ መላእክት፣ የመላእክት አለቆች፣ ጻድቃን ሰማዕታትም እየሰገዱላትና ፈጽሞ እያመሰገኗት አሳረጓት፡፡ ቅዱስ ዳዊትም ‹‹ንግሥት እመቤታችን! ወርቀ ዘቦ ለብሳ ደርባ ደራርባ በቀኝህ ትቀመጣለች›› እያለ በበገና አመሰገናት፡፡