Перейти к содержимому

🔴“አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነስ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት፡” መዝ.131÷8 Psalm 131 no 8

ከርቤ ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙራት፣ምክረ አበው፣ሃይማኖታዊ ትረካና ጥቅሶች..

0:00 / 0:00

🔴“አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነስ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት፡” መዝ.131÷8 Psalm 131 no 8

115 просмотров · 1 месяц назад
ከርቤ ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙራት፣ምክረ አበው፣ሃይማኖታዊ ትረካና ጥቅሶች..
55 подписчиков
115 просмотров · 1 месяц назад
🔴 ይህንን ቻናል Subscribe በማድረግ አገልግሎቱን ይደግፉ።ለወዳጅዎም በማጋራት የእግዚአብሔር ቃል እንዲዳረስ የበኩልዎን ይወጡ። እግዚአብሔር ያክብርልን!! “አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነስ፤ አንተና የመቅደስህ ታቦት፡፡” መዝ.131÷8 ክቡር ዳዊት ከላይ የተጠቀሰውን መዝሙር ለጊዜው ለባቢሎን ምርኮ ትሩፋን ወይም ቅሬታዎችና ለዘሩባቤል ተናግሮታል፡፡ ለፍጻሜው ግን ስለ እመቤታችን ትንሳኤ ገልጾበታል፡፡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጐ ተነስቶ እናቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሞታ አትቀርምና፤ አንተ ብቻ ሳትሆን አማናዊት የመቅደስህ ታቦት የተባለች እመቤታችንን ይዘህ ተነስ ሲል ነው፡፡ ዳሩ የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ የሁላችንም (የጻድቃንም የኃጥአንም) ትንሳኤ ነው፡፡ በመጨረሻው ዘመን የሰው ልጆት ሁሉ ከሞት ይነሳሉና፡፡ ታዲያ በጌታችን አማካኝነት ለሁሉ የተሰጠ ትንሳኤ ለእመቤታችን ቀድሞ መደረጉ ምን ያስደንቃል? የሚያስደንቀው የመለኮት እናት ሆና ሳለ ሞትን መቅመሷ ነው እንጂ፡፡ ለዚህም ነው ሊቁ “ሞትስ የሚሞትን ሥጋ ለለበሰ ሰው ይገባዋል፤ የድንግል ማርያም ሞት ግን ለሁሉም ይደንቃል፡፡” ያለው፡፡ እመቤታችን የመቅደሱ ታቦት ምሳሌ መሆኗን መረዳት አስፈላጊ ሲሆን፤ እንደሚከተለው ተብራርቷል፡፡