አንተ ለእኔ መልካም ነህ | Apostolic Church of Ethiopia | Apostolic songs
Iso Yisehak Ab
0:00 / 0:00
አንተ ለእኔ መልካም ነህ | Apostolic Church of Ethiopia | Apostolic songs
23 459 просмотров · 3 г. назад
Iso Yisehak Ab
36,4 тыс. подписчиков
23 459 просмотров · 3 г. назад
ከሚያዝያ 20-22/2015 የተካሄደው የሀዋሳ እናት አጥቢያ ሐዋሪያዊት ቤተክርስቲያን የጸሎት ቤት ምርቃት።
ግጥም/Lyrics
ለደካማው ካደረግኽልኝ መልካም ነገር ሁሉ
አንዱም እንኳን የሚገባኝ አይደለሁም
እኔን ለማዳን ስትረዳኝ ስታግዘኝ አያለሁ
አምላኬ የአንተን ብዙ ቸርነት ፍቅርህን ቀምሻለሁ
እግዚአብሔር |አንተ ለእኔ መልካም ነህ| 4x
1. በመልካሙ ጎዳና ነፍሴን በጽድቅ መንገድ ላይ
በማዳንህ ደግፈህ ልቤን ደስታ እየሞላህ
እጄን ይዘህ እየመራህ ውጣ ውረዱን ሁሉ
የእኔ ጌታ ታማኝ ነህ እግዚአብሔር በቃልህ
ከሠጠኸኝ ልስጥህ ጌታዬ
ከበረከትህ ምንጭ አባቴ
የአንደበቴን ፍሬ ምስጋና
እሰዋልሃለሁ እንደገና
እግዚአብሔር አንተ ለእኔ...
2. በልቤ የፈሰሰው ፍቅርህ እጅግ ብዙ ነው
ተናግሬ አመስግኜ ዘምሬ እንኳን አልዘልቀው
ለዋልክልኝ ውለታ የምሰጥህን ባጣ
መልካም ነህ እኔ እላለሁ ሁልጊዜ ጠዋት ማታ
ከሠጠኸኝ ልስጥህ...
3. አሳብህ እንደ አሳቤ አይደለችም አውቃለሁ
በእኔ ልትሰራ ያለው መልካሚቷን ነገር ነው
ስለዚህ በአንተ ጌታ ተማምኜ እኖራለሁ
ምንም አይጎድልብኝ ቤቴ በአንተ ሙሉ ነው
ለደካማው...