#እቀዳስ ዘንድ እፈልጋለሁ #Ethiopian apostolic
Abel official Tube
0:00 / 0:00
#እቀዳስ ዘንድ እፈልጋለሁ #Ethiopian apostolic
2 028 просмотров · 11 дн. назад
Abel official Tube
1,62 тыс. подписчиков
2 028 просмотров · 11 дн. назад
#ethiopian
እቀደስ ዘንድ እፈልጋለሁ
ሕይወቴን ኢየሱስ ሰጥቼሃለሁ
ቀድሰኝ፤ ቀድሰኝ ኢየሱስ ሆይ ቀድሰኝ
ቀድሰኝ፤ ቀድሰኝ በፈቃድህ ምራኝ አሜን
አንደበቴ ጽድቅህን ይናገር ዘውትር የምስራቹን ያውራ
ቀድሰኝና ምስክርህ ልሁን ኢየሱሴ ለሰራኸው ሥራ
የማትከብርበትን ከሕይወቴ አውጣና በጽድቅህ ሕያው አድርገኝ
በቤትህ ውስጥ ተክለህ አለምልመህ አላማህን ፈጽምብኝ
ተጠርቻለሁ ጌታዬ በስምህ እንግዲህ የአንተ ሆኛለሁ
በፊትህ አለሁ ያሻህን አድርገኝ ሕይወቴን ለአንተ ሰጥቻለሁ
ቅድስና ያብብ በእኔ ላይ ታጋሽም አድርገኝ ጌታዬ
ልቤም ኢየሱስ ዙፋንህ ይሁንና ላንግስህ በሁለንተናዬ
ፍለጋህን ልከተል አምላኬ አንተን እየመሰልኩኝ ልኑር
ከኃጥያት ልራቅ ፈቃድህን ላድርግ በውስጤ አኑር የእውነትን ፍቅር
ሥጋዬንም እየጎሰምኩኝ እንዳስገዛው ኃይልን ስጠኝ
ደስ የሚያሰኝህን እየመረመርኩኝ እንዳደርግ ደግፈኝ እርዳኝ
የሥጋዬን ፍሬ አውጣልኝና ሙላኝ የመንፈስህን ፍሬ
የእኔ አይደለሁም በደምህ ተገዝቼአለሁኝ ላንተው ነው መኖሬ
ቃልህንም ሰምቼ ልፈጽም እንድወድህ ኢየሱስ እርዳኝ
ቀዳሼና የእስራኤል ቅዱስ እባክህ ቀርበህ ቀድሰኝ