የአመጋገብ ስርዓትን በማሻሻል ጤናማ እና አምራች ዜጋ ማፍራት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ
Amhara Agriculture Bureau
0:00 / 0:00
የአመጋገብ ስርዓትን በማሻሻል ጤናማ እና አምራች ዜጋ ማፍራት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ
295 просмотров · 1 год назад
Amhara Agriculture Bureau
1,44 тыс. подписчиков
295 просмотров · 1 год назад
የአመጋገብ ስርዓትን በማሻሻል ጤናማ እና አምራች ዜጋ ማፍራት እንደሚያስፈልግ ተገለፀ
ባህርዳር፣ መጋቢት 25፣ 2017 ዓ/ም ( ግብርና ቢሮ ) የፌደራል ግብርና ሚኒስቴር ከአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ጋር በመተባበር የምርት ብክነትን ከመቀነስ፣ ጥራትና ደህንነትን ከማስጠበቅ አንጻር ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ብሄራዊ የምግብ ደህንነትና ጥራት፣ የድህረ ምርት አያያዝ እና የስርዓተ ምግብ ተኮር ግብርና ስትራቴጂዎችን የማስተዋወቅ የውይይት መድረክ ከባለድርሻ አካላት ጋር አካሂዷል።
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አጀበ ስንሻው ክልሉ በሰብል ልማት እና በእንስሳት ሀብት ከፍተኛ ምርት የሚመረትበት ቢሆንም ስርዓተ ምግብን በማረጋገጥ ረገድ ውስንነቶች ይታያሉ ብለዋል። የአመጋገብ ስርዓታችንን በመማሻሻል የተሰባጠረ የአመጋገብ ስርዓት በመከተል ጤናማ እና አምራች ዜጋ የማፍራት ሀላፊነታችንን መወጣት አለብን ብለዋል።
የምግብና ስርዓተ ምግብ ዋስትና መረጋገጥ ትውልድና ሀገር የመገንባት ጉዳይ ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል ያሉት አቶ አጀበ ስንሻው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር ዶ/ር ሐሚድ ጀማል በግብርናው ዘርፍ በምግብ ንጥረ ነገር የበለፀገ፣ ደህንነቱና ጥራቱ የተጠበቀ፣ የተሰባጠረና በቂ የምግብ አቅርቦት ተደራሽነትና ተጠቃሚነትን ለማሻሻል በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ተናግረው እነዚህን ስትራቴጂዎች በአግባቡ ተገንዝቦ ስራ ላይ ማዋል ያስፈልጋል ብለዋል።
በሀገራችን የድህረ ምርት አያያዝና የምርት ጥራት ላይ በትኩረት መስራት ለስርዓተ ምግብ መረጋገጥ የጎላ አበርክቶ እንዳለው የተናገሩት ዶ/ር ሐሚድ ጀማል ስትራቴጂውን እስከ አርሶ አደሮች ድረስ ማስተዋወቅ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ድምፅና ምስል ቅንብር ኤዲተር : ጌታቸው ታፈረ