Перейти к содержимому

የቅዳሜ ውዳሴ ማርያም አንድታ ትርጓሜ

Mahidere Sebhat Tihor Holy Trinity Church

0:00 / 0:00

የቅዳሜ ውዳሴ ማርያም አንድታ ትርጓሜ

146 просмотров · 1 мес. назад
Mahidere Sebhat Tihor Holy Trinity Church
161 подписчик
146 просмотров · 1 мес. назад
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን። የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የዐሥራት ልጆች፤ እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ። እነሆ በማኅደረ ስብሐት ትሆር ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ የዩቲዩብ ቻናል፣ በዚህ በተወደደ የሱባኤ ጊዜ የነፍስ ስንቅ የሚሆን መንፈሳዊ ማዕድ አሰናድተንላችኋል። ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ባዘጋጀውና መላእክትም አብረውት በቆሙበት "ውዳሴ ማርያም" በተሰኘው ታላቅ የጸሎትና የምስጋና መጽሐፍ፤ የድኅነታችን ምሥጢር፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋዌ እና የእመቤታችን ንጽሕና፣ ቅድስናና ድርብ ድንግልና በሰፊው ተብራርቶ ይገኛል።