Перейти к содержимому

Gospel Songs/ ፍቅር ነህ አሁንም| Apostolic Church of Ethiopia/ Hawassa

Iso Yisehak Ab

0:00 / 0:00

Gospel Songs/ ፍቅር ነህ አሁንም| Apostolic Church of Ethiopia/ Hawassa

16 430 просмотров · 5 л. назад
Iso Yisehak Ab
36,4 тыс. подписчиков
16 430 просмотров · 5 л. назад
በአዋሳ ቅ/ሰበካ የመሃል አዋሳ ንዑስ ሰበካ መዘምራን ከሐምሌ 09-11/2013 በአዋሳ እናት አጥቢያ በተዘጋጀ ጉባዔ የቀረበ መዝሙር ግጥም/Lyrics ለዕንቆቅልሼ መጥቼ ለጥያቄዎቼ መልስ ጥበብህ አስደንቆኛል እስከማይቀርልኝ ነፍስ ከነገሩኝ ከሰማሁት ከአየሁት እጅግ ይበልጣል ኢየሱስ ከሁሉ በላይ ነህ ፍቅርህ ልቤን ማርኮታል 1. ብዙ ነበረ በልቤ ያለው ማጫውትህ እንድትፈታልኝ የምፈልገው የምለምንህ ግን ፊትህ ስቆም መልካምነትህን ሳስተውለው ዕንቆቅልሼን ችግሬን ሁሉ ያኔ ረሳሁ ፍቅር ነው ሲገለጥ ማንነትህ ሲፈለግ በጸሎት ምልጃ ፊትህ ያስረሳል የሚናወጠውን ሁሉ ምቾት ነው ኢየሱስ ከአንተ ጋር መዋሉ 2. ከሽቱ በላይ ከከበረ ዕንቁ አስበልጬ በልቤ ከአለው ከመልካም ነገር ሁሉ መርጬ የነፍሴን መስዋዕት መርቼ ሰዋልሃለሁ በየማለዳው ስምህን ዘውትር እባርካለሁ ፈታኸው ስውር ነገሬን ኢየሱስ ሽቶዬ ምስጋናዬ ለአንተ ይፍሰስ በፍጹም አሳቤ ወድጄሃለሁ ዘለዓለም በፍቅርህ እገዛልሃለሁ 3. በፊትህ ቆመው ከሚያገለግሉ ጋር ዕድል አግኝቼ ምስጉን ተብዬ እንድቆጠር ከዕርስትህ ወገን ከቅዱስ ሕዝብ ለቀላቀልከኝ የማልሰስተው በልቤ የሞላ ምስጋና አለኝ ውሰደው የእኔ የምለውን ነገር በሕይወቴ በዘመኔ ሁሉ ክበር ፍቅር ነህ አሁንም እቀርብሃለሁ በፍጹም ኃይሌ ዘምርልሃለሁ የአፌን ነገር የሰማኸኝ ከመልካምነት ያጠገብኸኝ ስለውለታህ ምን መልሳለሁ በምስጋናዬ አከብርሃለሁ በምስጋናዬ አከብርሃለሁ በዝማሬዬ አነግስሃለሁ በእልልታዬ አከብርሃለሁ ስለውለታህ ምን መልሳለሁ