የስምንተኛው ሳምንት እርግዝና ምልክቶች እና የፅንሱ እድገት | The symptoms of 8 week pregnancy and fetus growth
ጤና Cure
0:00 / 0:00
የስምንተኛው ሳምንት እርግዝና ምልክቶች እና የፅንሱ እድገት | The symptoms of 8 week pregnancy and fetus growth
28 500 просмотров · 3 г. назад
ጤና Cure
203 тыс. подписчиков
28 500 просмотров · 3 г. назад
የልጃችሁ እድገት በዚህ ሳምንት የእጆቹ እና እግሮቹ ጥቃቅን ጣቶች እየተፈጠሩ ነው። እናም እጆቹ በክርን እና የእጅ አንጓዎች ላይ መታጠፍ ይችላሉ። በዚህ ጊዜ አይኖቹ ቀለም ማዳበር ይጀምራሉ እና የጾታ ብልቶቹም እንዲሁ ይፈጠራሉ, በዚህ ጊዜ ፆታውን መገመት የሚቻል ይሆናል።
ውጫዊ ገፅታው ብቻ አይደለም በማደግ ላይ ያሉት የውስጥ አካላቱም እንዲሁ እድገቶችን ያደርጋሉ። አንጀቱ በዚህ ጊዜ በሚፈጠርበት ሰዓት በልጁ ሆድ እቃ ውስጥ በቂ ቦታ ስለሌለ ከእትብቱ ውስጥ ቦታ መያዝ ይጀምራል። በዚህ የመጀመሪያ ደረጃ ላይ እንኳን, አንጀቱ ቆሻሻን ከሰውነት ለማስወገድ እየሰራ ነው።
ከአንድ ወር በኋላ, በትንሽ ልጃችሁ ሆድ ውስጥ ብዙ ቦታ ሲኖር, አንጀቱ ከ እትብቱ ወጥቶ ወደ ሆዱ ይመለሳል። በ 8 ሳምንታት እርግዝና ፅንሱ ብዙም ሳይቆይ, እድገቱ በፍጥነት ይጨምራል። ልጃችሁ በዚህ ሳምንት የኢንጆሪ ፍሬ መጠን ያክል ነው ማለትም ከ 0.5 እስከ 0.6 ኢንች ርዝማኔ አለው።
የስምንት ሳምንታት እርጉዝ በምትሆኑበት ጊዜ የእርግዝና ምልክቶች በከፍተኛ ፍጥነት ይጨምራሉ። ልብሶቻችሁ ትንሽ ያዝ ማድረግ ሊጀምሩ ይችላሉ። ደስ የማይል ምልክቶች ሊያጋጥሟችሁ ይችላሉ። ማወቅ ያለባችሁ ነገር በሁሉም ሴቶች ላይ የእርግዝና ምልክቶች የተለያየ ነው። ሁሉም እርግዝና አንድ አይደለም። እርግዝና በእያንዳንዱ ሴት ላይ የተለያየ ነው።
📌 የ 8 ሳምንታት እርግዝና ምልክቶች
በስምንት ሳምንት ነፍሰ ጡር ጊዜ፣ ሊያጋጥሙአችሁ የሚችሉ አንዳንድ ምልክቶች አሉ። እነዚህም፡-
➣የጠዋት ህመም ፦ የማቅለሽለሽ ስሜትን እና እንዲያውም ማስመለስ በዚህ ሳምንትም የሚያጋጥማችሁ ይሆናል። ጥሩ ጎኑ እነዚህ የህመም ስሜት ምልክቶች ከ አራተኛው ወራችሁ ጀምረው ይቀንሳሉ።
➣ የምግብ እና የማሽተት ጥላቻ
ከዚህ በፊት የማይረብሿችሁ አንዳንድ ጣዕም እና ሽታዎች አሁን ላይ ሊረብሿችሁ ይችላሉ። ይህም የሚሆነው በሆርሞኖች መጨመር ምክንያት ነው።
➣ ተቅማጥ
የምግብ መፍጫ ስርዓታችሁ አሁን የበለጠ ስሜታዊ ሊሆን ይችላል። ጤናማ የአመጋገብ መመገብ እና በቂ ውሃ መጠጣት የሚኖርባችሁ ይሆናል። ተቅማጥ ከ 24 ሰአታት በላይ የሚቆይ ከሆነ ወይም ከሌሎች ምልክቶች ጋር አብሮ ከሆነ ህክምና ማድረግ ይኖርባችኋል።
➣ በተደጋጋሚ የሽንት መሽናት
አሁንም በዚህ ጊዜ በተደጋጋሚ መሽናት ሊያጋጥማችሁ ይችላል። በተለይም ደግሞ ፅንሱ ሲያድግ እና ማህፀናችሁ እየሰፋ በሚሄድበት ጊዜ ይህ ምልክት በቀሪው እርግዝናችሁ ውስጥ የሚያጋጥማችሁ ይሆናል።
➣ የሆድ ቁርጠት.
ይህ ምልክት ከማህፀናችሁ ቀጣይ እድገት ጋር ሊዛመድ ይችላል።ነገር ግን ቁርጠቱ ከባድ ከሆነ ችግሮችን ለማስወገድ በአፋጣኝ ህክምና ማድረግ የሚኖርባችሁ ይሆናል።
➣የጀርባ ህመም
የስምንት ሳምንታት እርጉዝ በምትሆኑበት ጊዜ የጀርባ ህመም ሊገጥማችሁ ይችላል።በተለይም በታችኛው ጀርባችሁ አካባቢ። ክብደታችሁ እያደገ በሚሄድበት ጊዜ ማህፀናችሁን ለማስተናገድ በጀርባችሁ በኩል ያሉት ጡንቻዎች ከወትሮው በበለጠ ስለሚሰሩ ነው።
➣ የ ነጠብጣብ የደም መፍሰስ.
ነጠብጣብ ደም መፍሰስ መደበኛ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን፣ የጭንቀት መንስኤ ከሆነ ህክምና ማድረግ የሚኖርባችሁ ይሆናል።
➣ ድካም
በእርግዝና ጊዜያችሁ የፕሮጄስትሮን መጠን እየጨመረ ስለሚሄድ ከወትሮው የበለጠ ድካም እንዲሰማችሁ ሊያደርግ ይችላል።
➣ የመተኛት ችግር
የሆርሞን ደረጃዎች መለወጥ, ምቾት ማጣት እና ወደ መጸዳጃ ቤት መመላለስ ብዙውን ጊዜ የ እንቅልፍ መረበሽን ይጨምራሉ። ስለዚህም ከመተኛታችሁ በፊት ሞቅ ያለ ወተት መጠጣት ወይም ገላችሁን ሰላማዊ እንቅልፍ እንድታገኙ ይረዳችኋል። ለ አንዳንድ ሴቶች ደግሞ በግራ ጎናቸው መተኛት ጠቃሚ ነው። ምክንያቱም የደም ዝውውርን ያሻሽላል። እንዲሁም ትራስ በጉልበቶቻችሁ መካከል ማስቀመጥ የበለጠ ምቾት እንዲሰማችሁ ያደርጋል።
📌 የ 8 ሳምንታት እርግዝና: ሊታሰብባቸው የሚገቡ ነገሮች
➣የሚለጠጡ እና ምቾት ያላቸውን ልብሶች መልበስ ይኖርባችኋል።እንዲሁም ከዚህ በኋላ ጠባብ ሱሪዎችን መልበስ የለባችሁም።
➣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ እንክብካቤ ማድረግ ይኖርባችኋል። ከእርግዝናዎ በፊት በትክክል ንቁ መሆን እና ጥሩ እንክብካቤ ማግኘት አስፈላጊ ነው።
➣ተገቢውን የፅንስ ክትትል ማድረግ የሚኖርባችሁ ይሆናል።
#እርግዝና
#education
#health