Перейти к содержимому

ብሄራዊ ባንክ ያሳለፈው ውሳኔ! ግሽበቱን ለመቀልበስ ምን ታቀደ? | Decision Passed by the NBE!

Gebeya Media - ገበያ

0:00 / 0:00

ብሄራዊ ባንክ ያሳለፈው ውሳኔ! ግሽበቱን ለመቀልበስ ምን ታቀደ? | Decision Passed by the NBE!

2 187 просмотров · 14 ч назад
Gebeya Media - ገበያ
669 тыс. подписчиков
2 187 просмотров · 14 ч назад
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ኮሚቴ ያካሄደውን ስምንተኛ መደበኛ ስብሰባ ተከትሎ በትላንትናው እለት ይፋ ያደረገው መረጃ የሀገሪቱን የማክሮ ኢኮኖሚ አጠቃላይ ሁኔታ፣ የዋጋ ግሽበት አዝማሚያዎችን እና የወደፊት የፖሊሲ አቅጣጫዎችን በጥልቀት የሚመረምር ወሳኝ ምዕራፍ ነው። እንደ ብሔራዊ ባንክ ግምገማ ከሆነ በቅርብ ወራት ውስጥ የተመዘገበው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ከበፊቱ በትንሹ መሻሻል ቢያሳይም፣ አሁንም ከባንኩ የረጅም ጊዜ የነጠላ አሃዝ ግብ አንጻር ከፍተኛ መሆኑን ያመለክታል። ባንኩ ባወጣው መረጃ መሠረት በመስከረም ወር 2019 ዓ.ም የተመዘገበው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 14.9 በመቶ ደርሷል። ይህ አኃዝ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ አሁንም ከውስጣዊ እና ውጫዊ የዋጋ ግፊት ጋር መጋፈጡን በግልጽ ያሳያል። የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ እንደገለጹት የዋጋ ግሽበቱ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ የተወሰነ የመቀነስ አዝማሚያዎችን እያሳየ ቢሄድም፣ ሙሉ በሙሉ ከድርብ አሃዝ ወርዶ ወደ ነጠላ አሃዝ ግን ሊገባ እንደማይችል እና በድርብ አሃዝ ውስጥ ጸንቶ እንደሚቀጥል ተነግሯል። ይህ ትንበያ የኢትዮጵያን የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበት ተግዳሮቶች ዘላቂ መፍትሄ ለማግኘት ሰፊ እና የተቀናጀ የፖሊሲ ማሻሻያ ሥራዎች አሁንም እንደሚጠይቁ ያሳያል። በተለይም የዋጋ ግሽበቱ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ውስጥ በድርብ አሃዝ ውስጥ ጸንቶ እንደሚቆይ መገለጹ፣ የኢኮኖሚ ባለሙያዎችን እና መላውን የሀገሪቱን ማህበረሰብ ቀልብ የሳበ ዋናው ጉዳይ ሆኖ ተነስቷል። በእለቱ የገበያ ቢዝነስ ልዩጥንቅራችንም የብሄራዊ ባንክ የዋጋ ግሽበቱን አስመልክቶ ይፋ ያደረገውን መረጃና ሌሎች ተያያዥ ቁልፍ ጉዳዮችን አንድምታ፣ የዋጋ ግሽበቱ ትንበያ ለተራው ዜጋ ላይ ምን ማለት ነው? እየተተገበረ ስላለው ሪፎርም ምን ይነግረናል እንዲሁም የዋጋ ግሽበቱን ለመግታት ምን አይነት መፍትሄ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል? የሚሉትንና ተያያዥ ጉዳዮችን እንመለከታለን ፡፡ አብራችሁን ቆዩ፡፡ Following the National Bank of Ethiopia's Monetary Policy Committee eighth regular meeting, the information released to the public yesterday marks a crucial milestone in deeply examining the country's overall macroeconomic situation, inflation trends, and future policy directions. According to the National Bank's evaluation, while the headline inflation recorded in recent months has shown a slight improvement compared to the past, it still remains significantly high relative to the bank's long-term single-digit target. Based on the data released by the bank, the headline inflation rate recorded in September 2026 reached 14.9%. This figure clearly indicates that the Ethiopian economy is still grappling with internal and external inflationary pressures. As noted by the Governor of the National Bank, Dr. Eyob Tekalign, although inflation is expected to show some downward trends over the next six months, it will not fully drop out of double digits into a single-digit figure, but rather persist within the double-digit range. This projection shows that achieving sustainable solutions to Ethiopia's cost-of-living and inflation challenges still requires broad and coordinated policy reforms. In particular, the announcement that inflation will remain entrenched in the double digits over the next six months has emerged as a major talking point, capturing the attention of economic experts and the wider public alike. In our special business market analysis of the day, we explore the implications of the National Bank’s released inflation data and other key related issues: What does the inflation projection mean for the ordinary citizen? What does it tell us about the ongoing reforms? And what solution directions have been set to curb inflation? Stay with us as we delve into these topics and more. #GebeyaMedia #GebeyaBusiness #GebeyaSpecialProgram #GebeyaNews #GebeyaAnalysis #NationalBankOfEthiopia #EthiopianEconomy #Inflation #Macroeconomics #MonetaryPolicy #CostOfLiving #EthiopiaBusiness #EconomicReform #FinancialNews