📢 ጻድቁ ዓባ ያሳይ#የጻድቅ መታሰቢያለዘላለም ይኖራል"መዝሙር 111፤6
Kerbe tube
0:00 / 0:00
📢 ጻድቁ ዓባ ያሳይ#የጻድቅ መታሰቢያለዘላለም ይኖራል"መዝሙር 111፤6
16 просмотров · 6 дн. назад
Kerbe tube
592 подписчика
16 просмотров · 6 дн. назад
እንኳን አደረሰን
"የጻድቅ መታሰቢያ
ለዘላለም ይኖራል።"
መዝሙር 111፤6
መስከረም 14 ቀን
ኮከበ ገዳም
መናኔ መንግሥት
የንጉሥ ዐፄ ዓምደ ጽዮን ልጅ
ባለ ብዙ ገድል የበረከት አባት
የ ጣናን ባሕር በድንጋይ ታንኳ የተሻገሩት የደብረ በንኮል መናኝ የታላቁ ጻድቁ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ የቆብ ልጅ የማን እንዳባ መድኃኔዓለም ገዳሙ ባሕታዊ
የጻድቁ አቡነ ያሳይ በዓለ ዕረፍታቸው ነው።
በነገራችን ላይ አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዜና ገድላቸውን ሰምተው ከምድረ ሸዋ እና ትግራይ አክሱም ደብረ በንኩል የመጡትን አባ ያሳይ እና ስድስቱን ደቀመዛሙርት ልጆቻቸው በአንድ ቀን ነው ያመነኮሷቸው።
7ቱ ከዋክብት እየተባሉ ይጠራሉ።
እነሱም
አቡነ ያሳይ ማን ዘእንዳባ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ
አቡነ አብሳዲ ዘዞዝ አንባ አቡነ ያፈቅረነ እግዚእ ዘጉጉቤን
አቡነ ሳሙኤል ዘቆየጻ አቡነ ዮሐንስ ዘግራናቔ
አቡነ ሳሙኤል ዘጣሬጣ ይባላሉ።
መነኮሳት እናታቸው ድንግል ማርያም አባታችው እግዚአብሔር ነውና ከመነኮሱ በኋላ በገዳማቸው ስም ነው የሚጠሩ የአባት ስም ተክተው በጥንቱ ወንዝና ተራራ አይቆጥሩም በብሔር ከረጢት አይቋጠሩም መነኮሰ ሞተ ነውና።
የቆብ አባቶቻቸውን ነው መነኮሳት የሚቆጥሩ አቡነ ያሳይ በቆብ 9ኛ ናቸው።
ርዕሰ አበው ዓመደ መነኮሳት
አባ እንጦንስ አባ መቃርስን አባ መቃርስ አባ ጳኩሚስን
አባ ጳኩሚስ አባ ቴዎድሮስን አባ ቴዎድሮስ አባ አረጋዊን(ዘሚካኤልን)
አባ አረጋዊ አባ ማትያስን አባ ማትያስ አባ ዮሴፍን
አባ ዮሴፍ አባ መድኃኒነ እግዚእን
አባ መድኃኒነ እግዚእ አባ ያሳይን እና ሌሎች አበውን አመንኩሰዋል።
በባሕረ ጣና የሚገኘው የጻድቁ መካነ ማን እንዳ አባ መድኃኔዓለም ገዳም እስከ ዘመናችን በርካታ ቅዱሳን አበው የወጡበት ገዳም ነው።
መነኮሳቱ የጥንቱን ቤተክርስቲያን በአስደናቂ ሁኔታ አድሰውታል እግዚአብሔር አምላካችን አጽራረ ገዳማት አጽራረ ቤተክርስቲያንን ያስታግስልን አምላከ አበው ከዘረኝነት ደዌ ከፍቅር ረሐብ ከዝሙት እሳት ከክሕደት አሽክላ ይሰውረን አሜን አሜን አሜን