Перейти к содержимому

የህወሃት 5 ከፍተኛ አመራሮች በድሮን ተደመሰሱ፤ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከአባይ እና ከቀይ ባህር ጋር የተያያዘውን ቁምነገር አወጡ!

Abri Media አብሪ ሚዲያ

0:00 / 0:00

የህወሃት 5 ከፍተኛ አመራሮች በድሮን ተደመሰሱ፤ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከአባይ እና ከቀይ ባህር ጋር የተያያዘውን ቁምነገር አወጡ!

9 516 просмотров · 14 ч назад
Abri Media አብሪ ሚዲያ
19,5 тыс. подписчиков
9 516 просмотров · 14 ч назад
በዛሬው የአብሪ ሚዲያ መርሃ ግብር የተመረጡ ወቅታዊ እና ትኩስ የሀገር ውስጥ ዜናዎችን ይዘን አቅርበናል፡- የመከላከያ ሰራዊት ድል በዛና: የሀገር መከላከያ ሰራዊት በዛና አካባቢ በወሰደው ጠንካራ ማጥቃት እርምጃ የህወሃት ታጣቂ ሃይልን በመምታት በርካታ የጦር መሳሪያዎችን፣ መድፎችን፣ ሞርተሮችን፣ ሮኬቶችን እና 15 ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን መማረኩ ተገለጸ። የህወሃት አመራሮች በድሮን መደምሰስ: በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር በኩል በጭነት ተሽከርካሪ ተጭነው ሊያመልጡ ሲሞክሩ በስለላ ድሮኖች ሲጠበቁ የነበሩ ቢያንስ አምስት ከፍተኛ የህወሃት ወታደራዊ አመራሮች በድሮን ጥቃት ተደምስሰዋል። የሞያሌው ቀውስ እና የሰርጎ ገቦች መያዝ: በሞያሌ ከተማ በኦሮሞ እና በሶማሌ ህዝቦች መካከል የውሸት መረጃዎችን በማሰራጨትና ቀውስ ለመፍጠር የሞከሩ፣ እንዲሁም የሶማሊያ አዛውንቶችንና ሴቶችን የገደሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል። ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ መግለጫ: ከአባይ ውሃ እና ከቀይ ባህር የሚገኘውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ከማስከበር ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለ የገለጹት የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፤ የውስጥ ባንዳዎችን እና የውጭ ጠላቶችን ሴራ አጋልጠዋል። የባህርዳር ሰላማዊ ሁኔታ: በባህር ዳር ከተማ አለም አቀፍ ጉባኤዎች እና የልማት ስራዎች መመረቃቸው የጽንፈኛውን ቡድን የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ሙሉ በሙሉ የሚያጋልጥ መሆኑ ተጠቁሟል። #AbriMedia #አብሪሚዲያ #EthiopiaNews #ኢትዮጵያ #Ethiopia #ENDF #TPLF #BerhanuJula #EthiopianDefense #Moyale #BahirDar #RedSea #Abbay #NewsUpdate