Перейти к содержимому

4 እፈልግሃለሁ | ምስጋናዬ አማረ | EFELGHALEHU | MISGANAYE AMARE | EP Album Volume 1 / 2018/2026

Misganaye Amare

0:00 / 0:00

4 እፈልግሃለሁ | ምስጋናዬ አማረ | EFELGHALEHU | MISGANAYE AMARE | EP Album Volume 1 / 2018/2026

8 865 просмотров · 10 дней назад
Misganaye Amare
946 подписчиков
8 865 просмотров · 10 дней назад
እፈልግሃለሁ ከዕለት ተዕለቱ ተግባሬ - ጉዳዬ ካልኩት ነገሬ ከከበበኝም በሙሉ - ስሚኝ ከሚለኝ ድምፅ ኹሉ በማያቋርጥ ሰንሰለት - ነፍሴን ጠርቆ ሊይዛት ከሚሻው ማልዶ ሊያጠምደኝ - በድግግሞሽ ሊያስቀረኝ አንተንና መንግስትህን አስቀድሜ ከእግርህ ስር መሆንን ልምረጥ ደጋግሜ ትኩረት ንሳው ያልኸኝን ብዬው ችላ ዋና ሳይኖረኝ ቀዳሚ ካንተ ሌላ እፈልግሃለሁ/3 ኢየሱስ እፈልግሃለሁ ህይወት ነው አንተን መፈለግ - ሳይታክቱ ኢየሱስ ማለት ለጉዳዬ ስኬት ሳይሆን - ራስህ ጉዳዬ ስትሆን የፀሎት ርዕስም ባይኖረኝ - ከእግሮችህ ስር ፈልጌህ ስገኝ የአባትና ልጅ ህብረቱ - ይህ አይደለም ወይ ውበቱ በእጅህ ካለው በላይ ፊትህን እየፈለግኹ ከምትሰጠኝ ይልቅ ሰጪው አንተን እየናፈቅኹ አደባባይ ጓዳዬ በአብሮነትህ እንዲሞላ በኑሮዬ እንድትበዛልኝ በህልውናህ እፈልግሃለሁ/3 ኢየሱስ እፈልግሃለሁ የሚያስፈልገው አንድ ነገር - የማይወሰድ መልካም ዕድል በሀሳብ በቃል በግብር - ዘወትር መፈለግ አንተን ብሮጥ ላንተ እኮ ነው ካልኩት - ያልወደድኽልኝ አገልግሎት እያባከነኝ ካለው አምልጬ - ልምጣ አንተኑ መርጬ ከመስዋዕቴ ከማደርገው ነገር ይልቅ የአንተ መሻት ተጠግቼህ አንተኑ እንዳውቅ የልብህን ደስታ ትኩረትህም ያለበትን አብልጬ ልውደደው ልከታተል አንተን መስማትን እፈልግሃለሁ/3 ኢየሱስ እፈልግሃለሁ እወደዋለሁ ድምፅህን - ናፍቀዋለሁ ፊትህን የህይወቴ ግብ ባንተ መመራት - አንተንም ሰምቶ መሰማራት እንድፈልግህ ትፈልጋለህ - በመፈለግም ደስ ትሰኛለህ ስፈልግህ እኔም በህይወት ኖራለሁ - ድምፅህን ሰምቼም አርፋለሁ ድምፅህ ይመራል - ድምፅህ ያሳርፋል ድምፅህ ያሰማራል - ድምፅህ ይወደዳል