3 የሰማይ እንጀራ | ምስጋናዬ አማረ | YESEMAY ENJERA | MISGANAYE AMARE | EP Album Volume 1 / 2018/2026
Misganaye Amare
0:00 / 0:00
3 የሰማይ እንጀራ | ምስጋናዬ አማረ | YESEMAY ENJERA | MISGANAYE AMARE | EP Album Volume 1 / 2018/2026
3 031 просмотр · 10 дней назад
Misganaye Amare
951 подписчик
3 031 просмотр · 10 дней назад
የሰማይ እንጀራ
ካንተ ወደ ማን ወደ ማን እሄዳለሁ
የህይወት እንጀራ ኢየሱስ አንተን አግኝቼአለሁ
ካንተ ወደ የት ወደ የት እሄዳለሁ
የህይወት ቃል ያለህ ኢየሱስ አንተኑ ይዤአለሁ
ወደ ማን አያለሁ ወዴትስ እሄዳለሁ
የህይወትን ትርጉም አንተን አግኝቼአለሁ/ አንተኑ ይዤአለሁ
ሰውማ በልቶ የሚሞት ስጋ ለባሽ
80 የተቀጠረለት ነው ፈራሽ
በአለም ኖረን እንዳንሞት ስትራራ
ሆንክልን ህያው የሰማይ እንጀራ
በመስቀል ላይ ሞተህ የቆረስኸውን ስጋህን በልቶ
ወደአንተ የሚመጣ አይራብም ከቶ
የአዲሱን ኪዳን ያፈሰስኸውን ደምህን የጠጣ
በአንተ አምኗልና ሁልጊዜም አይጠማ
ኢየሱስ ክርስቶስ የአለም መዳኛ
በፀጋህ በዕምነት ህይወት ሆነ ለእኛ
ከላይ ተመልክተህ መቅበዝበዛችንን
ዕረፍት እንኩ አልኸን ወስደህ ሸክማችንን
መናውን በምድረበዳ የበሉቱ
ከምድር የሆነውን ውሃም የጠጡቱ
አባቶች ምድረበዳው ላይ እንደሞቱ
ያመንንብህ ፍፃሜአችን አይደል የከንቱ
ከምድሩ ያለፈ የዘለአለምን ህይወት ተስፋ
በስምህ አገኘን እጅህም ያዘን እንዳንጠፋ
ባንተ ያመንን ሁሉ ተቸርን ፅኑ ብርቱ ዋስትና
ወደአንተ የሚመጣን ወደውጪ አታወጣውምና
ኢየሱስ ክርስቶስ መልካሙ እረኛ
ነፍስህን ስለበጎች ያኖርኽ የማትተኛ
ከአውሬው ከክፉው ከዚህ አለም ጠብቀህ
ፅዮን እንገባለን ከፊት ከፊት መርተህ