ከብድር የሚገላግለው አዲስ መመሪያ! ረቂቁ ምን አይነት መስፈርቶችን ይዟል? የሚፈቀድላቸውስ እነማን ናቸው? |ECMA Draft Crowfunding Funding!
Gebeya Media - ገበያ
0:00 / 0:00
ከብድር የሚገላግለው አዲስ መመሪያ! ረቂቁ ምን አይነት መስፈርቶችን ይዟል? የሚፈቀድላቸውስ እነማን ናቸው? |ECMA Draft Crowfunding Funding!
3 879 просмотров · 1 день назад
Gebeya Media - ገበያ
665 тыс. подписчиков
3 879 просмотров · 1 день назад
በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዙት አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች (SMEs) ለዘመናት ትልቁ ፈተናቸው ሆኖ የዘለቀው የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት ነው። ባንኮች ለብድር የሚያቀርቡት ጥብቅና ከባድ የዋስትና ፍላጎት፣ ረጅም ቢሮክራሲ እንዲሁም ከፍተኛ የወለድ ምጣኔ ለብዙ አዳዲስ አሳቦችና እያደጉ ላሉ ንግዶች ትልቅ እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል። ይህንን ሥር የሰደደ የፋይናንስ ችግር በጥበብ ለማቃለልና የካፒታል ገበያውን ተደራሽነት ወደታች ለማውረድ በሚል የኢትዮጵያ ካፒታል ማርኬት ባለስልጣን (ECMA) አዲስና ታሪካዊ ረቂቅ መመሪያ አዘጋጅቷል። ይህ "የክራውድፈንዲንግ መመሪያ (Crowdfunding Directive) የሕግ ማዕቀፍ፣ አነስተኛ ኩባንያዎች ባህላዊ ከሆነው የባንክ ሥርዓት ውጭ በዲጂታል የሕዝብ ተሳትፎ አማካይነት ካፒታል ማሰባሰብ የሚችሉበትን አስተማማኝና ዘመናዊ በር የሚከፍት ነው። የኢትዮጵያ ካፒታል ማርኬት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በቅርቡ በሰጡት መግለጫ “የካፒታል ገበያው ለትላልቅ ኩባንያዎችና ለግዙፍ ባንኮች ብቻ የተወሰነ አይደለም፤ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሀገሪቱ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት በመሆናቸው ቀጥተኛ የካፒታል ማሰባሰብ ዕድል ሊኖራቸው ይገባል” በማለት የዚህን አሰራር አስፈላጊነት አብራርተዋል።
በእለቱ የገበያ ቢዝነስ ዝግጅታችንም ይህ የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስጣን ያዘጋጀው ረቂቅ በህዝብ ተሳትፎ የሚሰበሰብ ካፒታል መመሪያ ወይም Crowdfunding Directive ለኢትጵያ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ላለቸው ተቋማት ምን ይዟል? በረቂቅ መመሪያው የተካተተቱ አስገዳጅ መስፈርቶች ምንድናቸው? የሚፈቀድላቸው ተቋማትስ እነማን ናቸው? የሚሉትንና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን እንመለከታለን፡፡
ቻናላችንን ሰብስክራይብ ፣ ይህንን ቪድዮ ላይክና አስተያያት ካላችሁ ደግሞ ኮሜንት እያደረጋችሁ አብራችሁን ትቆዩ ዘንድ እንጋብዛለን፡፡
Small and Medium Enterprises (SMEs), which hold the largest share of Ethiopia's economy, have long faced financing shortages as their biggest challenge. Strict and heavy collateral requirements imposed by banks, lengthy bureaucracy, and high interest rates have remained major obstacles for many new ideas and growing businesses. To wisely alleviate this deep-rooted financial problem and bring capital market accessibility down to the grassroots level, the Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) has drafted a new and historical directive. This "Crowdfunding Directive" legal framework opens a reliable and modern door for small companies to raise capital through digital public participation outside the traditional banking system. In a recent statement, the Director General of the Ethiopian Capital Market Authority highlighted the importance of this framework, stating, “The capital market is not reserved only for large corporations and giant banks; as SMEs are the backbone of the country’s economy, they must have direct access to capital-raising opportunities.”
In today’s Special Business program, we will explore what this Crowdfunding Directive drafted by the Ethiopian Capital Market Authority holds for Ethiopia’s small and medium-sized enterprises. What are the mandatory requirements included in the draft directive? Which institutions are eligible to participate? We will examine these and other related issues.
We invite you to stay with us by subscribing to our channel, liking this video, and dropping your thoughts in the comment section.
#GebeyaMedia #GebeyaBusiness #GebeyaBusinessNews #Ethiopia #EthiopianCapitalMarket #ECMA #Crowdfunding #SMEs #EthiopianEconomy #CapitalMarket #BusinessNews #EthiopianBusiness #FinancialInclusion